ዳንኤል 2:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ለኮከብ ቈጣሪዎቹ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ሕልሙንና ትርጕሙን ባትነግሩኝ አካላችሁ እንዲቈራረጥና ቤቶቻችሁም የፍርስራሽ ክምር እንዲሆኑ ወስኛለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም እንዲህ አላቸው፦ “መጀመሪያ ሕልሜን፥ ቀጥሎም ትርጒሙን ንገሩኝ፤ አለበለዚያ ግን እጅና እግራችሁ እንዲቈራረጥና ቤታችሁ የፍርስራሽ ክምር እንዲሆን ወስኛለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም መለሰ ከለዳውያኑንም፦ ነገሩ ከእኔ ዘንድ ርቆአል፥ ሕልሙንና ፍቺውን ባታስታውቁኝ፥ ትቈረጣላችሁ ቤቶቻችሁም የጕድፍ መጣያ ይደረጋሉ። |
ደግሞም ይህን ትእዛዝ የሚለውጥ ማንም ሰው ቢኖር፣ ከቤቱ ምሰሶ ተነቅሎ በምሰሶው ላይ እንዲሰቀል፣ ስለ ወንጀሉም ቤቱ የቈሻሻ መጣያ እንዲሆን አዝዣለሁ።
ስለዚህ እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅ፣ በሚሳቅና በአብደናጎ አምላክ ላይ ማንኛውንም ቃል የሚናገሩ ሕዝቦችም ሆኑ ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሁሉ ይቈራረጣሉ፤ ቤቶቻቸውም የፍርስራሽ ክምር ይሆናሉ ብዬ አዝዣለሁ።”
እኔም እንዲህ አልሁት፤ “የጠቢባን አለቃ ብልጣሶር ሆይ፤ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ ውስጥ እንዳለ ዐውቃለሁ፤ ምንም ዐይነት ምስጢር አያስቸግርህም፤ ያየሁት ሕልም እነሆ፤ ተርጕምልኝ።
በከተማዪቱ የተገኘውን የምርኮ ዕቃ ሁሉ በአደባባይዋ መካከል ላይ ሰብስበህ፣ ከተማዪቱን ከነምርኮዋ እንዳለ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ በሙሉ አቃጥል። ለዘላለም እንደ ፈረሰች ትቅር፤ ተመልሳም አትሠራ።
በዚያ ጊዜም ኢያሱ፣ እንዲህ ሲል ማለ፤ “ይህች ከተማ ኢያሪኮን መልሶ የሚሠራት ሰው በእግዚአብሔር ፊት የተረገመ ይሁን፤ “መሠረቷን ሲጥል፣ የበኵር ልጁ ይጥፋ፤ ቅጥሮቿንም ሲያቆም፣ የመጨረሻ ልጁ ይጥፋ” ብሎ ማለ።
ሳሙኤልም፣ “ሰይፍህ ሴቶችን ልጅ አልባ እንዳደረገቻቸው፣ እናትህም በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች” ሲል አጋግን ጌልገላ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ቈራረጠው።