ለመሆኑ ከዐምሳው ጻድቃን ዐምስት ቢጐድሉ በዐምስቱ ሰዎች ምክንያት መላ ከተማዋን ታጠፋለህን?” እርሱም፣ “አርባ ዐምስት ጻድቃን ባገኝ አላጠፋትም” አለ።
ዳንኤል 2:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱና ጓደኞቹ ከቀሩት የባቢሎን ጠቢባን ጋራ እንዳይገደሉ፣ የሰማይ አምላክ ምሕረት ያደርግላቸውና ምስጢሩንም ይገልጥላቸው ዘንድ እንዲጸልዩ አሳሰባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ከቀሩት የባቢሎን ጠቢባን ጋር እንዳይገደሉ የሰማይ አምላክ ምሕረት እንዲያደርግላቸውና ምሥጢሩንም እንዲገልጥላቸው ይለምኑት ዘንድ አሳሰባቸው። |
ለመሆኑ ከዐምሳው ጻድቃን ዐምስት ቢጐድሉ በዐምስቱ ሰዎች ምክንያት መላ ከተማዋን ታጠፋለህን?” እርሱም፣ “አርባ ዐምስት ጻድቃን ባገኝ አላጠፋትም” አለ።
ምናልባት ሕያው አምላክን ይገዳደር ዘንድ ጌታው የአሦር ንጉሥ የላከውን የጦር አዛዡን ቃል እግዚአብሔር አምላክህ ይሰማ ይሆናል፤ እግዚአብሔር አምላክህም ሰምቶ ይገሥጸው ይሆናል፤ ስለዚህ አንተም በሕይወት ለተረፉት ቅሬታዎች ጸልይ።’ ”
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እንደ ገና ለእስራኤል ቤት ልመና ዕሺ እላለሁ፤ ይህንም አደርግላቸዋለሁ፤ ሕዝባቸውን እንደ በግ መንጋ አበዛዋለሁ፤
የአባቶቼ አምላክ ሆይ፤ አመሰግንሃለሁ፤ አከብርሃለሁም፤ ጥበብንና ኀይልን ሰጥተኸኛልና፤ ከአንተ የጠየቅነውን ነገር አሳውቀኸኛል፤ የንጉሡን ሕልም አሳውቀኸናል።”
“እስኪ ንገሩኝ፤ አንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩትና ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋበት፣ ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ላይ ትቶ የጠፋውን ለመፈለግ አይሄድምን?
ጴጥሮስን ወህኒ ቤት ካስገባው በኋላ፣ አራት አራት ወታደሮች እየሆኑ እንዲጠብቁት በአራት ፈረቃ ለተመደቡ ወታደሮች አስረከበው፤ ይህን ያደረገውም የፋሲካ በዓል ካለፈ በኋላ ሕዝብ ፊት አውጥቶ ሊያስፈርድበት ዐስቦ ነው።
ወንድሞች ሆይ፤ ስለ እኔ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ የተጋድሎዬ አጋር እንድትሆኑ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በመንፈስ ፍቅር እለምናችኋለሁ።
ጌታ፣ በእውነት እያመለኩት የሚኖሩትን ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸውና ዐመፀኞችን እየቀጣ ለፍርድ ቀን እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል።
ከአንበሳ መዳፍና ከድብ መንጋጋ ያዳነኝ እግዚአብሔር አሁንም ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል።” ሳኦልም፣ “ሂድ፤ እግዚአብሔር ካንተ ጋራ ይሁን” አለው።