2 ሳሙኤል 8:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም አንድ ሺሕ ሠረገሎች፣ ሰባት ሺሕ ፈረሰኞችና ሃያ ሺሕ እግረኞች ማረከበት። ቍጥራቸው መቶ የሆነ የሠረገላ ፈረሶች ብቻ ሲቀሩ ሌሎቹን በሙሉ ቋንጃቸውን ቈረጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም አንድ ሺህ ሠረገሎች፥ ሰባት ሺህ ፈረሰኞችና ሃያ ሺህ እግረኞች ማረከበት። ቁጥራቸው መቶ የሆነ የሠረገላ ፈረሶች ብቻ ሲቀሩ ሌሎቹን በሙሉ ቋንጃቸውን ቆረጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ከሀዳድዔዜር አንድ ሺህ ሰባት መቶ ፈረሰኞችንና ኻያ ሺህ እግረኛ ወታደሮችን ማረከበት፤ ሠረገላ ለመሳብ የሚያገለግሉ አንድ መቶ ፈረሶችን አስቀርቶ፥ የቀሩትን ፈረሶች በሙሉ ቋንጃቸውን ቈርጦ ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆኑ አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ከእርሱ ሺህ ሰረገላዎችን፥ ሰባት ሺህ ፈረሰኞችን፥ ሃያ ሺህም እግረኞችን ያዘ፤ ዳዊትም የሰረገለኛውን ፈረስ ሁሉ ቋንጃ ቈረጠ፤ ለራሱም መቶ ሰረገላዎችን ብቻ አስቀረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ከእርሱ ሺህ ሰባት መቶ ፈረሰኞች፥ ሀያ ሺህም እግረኞች ያዘ፥ ዳዊትም የሰረገለኛውን ፈረስ ሁሉ ቋንጃ ቈረጠ፥ ለመቶ ሰረገላ ብቻ አስቀረ። |
ሰሎሞን ሠረገሎችንና ፈረሶችን ሰበሰበ፤ እርሱም አንድ ሺሕ አራት መቶ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት ሺሕ ፈረሶች ነበሩት፤ እነርሱንም በሠረገላ ከተሞችና ንጉሡ ባለበት በኢየሩሳሌም ከተማ አኖራቸው።
ዳዊትም አንድ ሺሕ ሠረገላ፣ ሰባት ሺሕ ፈረሰኛና ሃያ ሺሕ እግረኛ ወታደር ማረከ፤ አንድ መቶ የሠረገላ ፈረሶች ብቻ አስቀርቶ የቀሩትን ቋንጃቸውን ቈረጠ።
ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ፤ ወይም ደግሞ የፈረሰኞችን ቍጥር ለመጨመር ሕዝቡን ወደ ግብጽ አይመልስ፤ እግዚአብሔር፣ “በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ” ብሏችኋልና።
እግዚአብሔር ኢያሱን፣ “እነዚህን ሁሉ ነገ በዚች ሰዓት እንደ ሙት አድርጌ፣ በእስራኤል እጅ አሳልፌ ስለምሰጣቸው አትፍራቸው። የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሠረገሎቻቸውንም ታቃጥላለህ” አለው።