2 ሳሙኤል 7:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሂድና ባሪያዬን ዳዊትን፣ ‘እንዲህ ብለህ ንገረው፤ እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤ የምኖርበትን ቤት የምትሠራልኝ አንተ ነህን? በለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሂድና አገልጋዬን ዳዊትን፥ ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘እኔ የምኖርበትን ቤተ መቅደስ የምትሠራልኝ አንተ ነህን?’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሂድና ለአገልጋዬ ለዳዊት እኔ ስለ እርሱ የምለውን እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘እኔ የምኖርበትን ቤተ መቅደስ የምትሠራልኝ አንተ ነህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሂድ ለባሪያዬ ለዳዊት ንገረው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አንተ የምኖርበትን ቤት አትሠራልኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሂድ፥ ለባሪዬ ለዳዊት ንገረው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ |
“ስለምትሠራው ስለዚህ ቤተ መቅደስ ሥርዐቴን ብትከተል፣ ፍርዴን በተግባር ብትገልጸው፣ ትእዛዞቼን ብትጠብቅና ብትመላለስባቸው ለአባትህ ለዳዊት የሰጠሁትን ተስፋ በአንተ እፈጽመዋለሁ፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ቤት የት ትሠሩልኛላችሁ? ይላል ጌታ፤ ወይስ ማረፊያ የሚሆነኝ ቦታ የት ነው?