እርሱም በሙሴ ፊት እንዲህ እያለ እያወጀ ዐለፈ፤ “እግዚአብሔር ርኅሩኅና ቸር አምላክ፣ እግዚአብሔር ለቍጣ የዘገየ፣ ፍቅሩና ታማኝነቱ የበዛ፣
2 ሳሙኤል 7:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላክ ነህ፤ ቃልህም የታመነ ነው፤ ይህንም መልካም ነገር ለማድረግ ለባሪያህ ተስፋ ሰጥተኸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላክ ነህ፤ ቃልህም የታመነ ነው፤ ይህንንም መልካም የተስፋ ቃል ለአገልጋይህ ሰጥተሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሁንም ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ አምላክ ነህ፤ ቃልህ ታማኝ ነው፤ እነሆ፥ አሁንም ይህን መልካም የተስፋ ቃል ለአገልጋይህ ሰጥተሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ አሁንም አንተ አምላክ ነህ፤ ቃልህም እውነት ነው፤ ይህንም መልካም ነገር ለባሪያህ ተናግረሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ አሁንም አንተ አምላክ ነህ፥ ቃልህም እውነት ነው፥ ይህንም መልካም ነገር ለባሪያህ ተናግረሃል። |
እርሱም በሙሴ ፊት እንዲህ እያለ እያወጀ ዐለፈ፤ “እግዚአብሔር ርኅሩኅና ቸር አምላክ፣ እግዚአብሔር ለቍጣ የዘገየ፣ ፍቅሩና ታማኝነቱ የበዛ፣