እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አጣድ ከተባለው ዐውድማ ሲደርሱ፣ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ምርር ብለው አለቀሱ፤ ዮሴፍም በዚያ ለአባቱ ሰባት ቀን ልቅሶ ተቀመጠ።
2 ሳሙኤል 6:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ናኮን ዐውድማ ሲደርሱም በሬዎቹ ስለ ተደናቀፉ፣ ዖዛ እጁን ዘርግቶ የእግዚአብሔርን ታቦት ያዘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ናኮን አውድማ ሲደርሱም በሬዎቹ ስለተደናቀፉ፥ ዖዛ እጁን ዘርግቶ የእግዚአብሔርን ታቦት ያዘ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናኮን ተብሎ ወደሚጠራውም አውድማ በደረሱ ጊዜ ሠረገላውን የሚስቡት በሬዎች ስለ ነቀነቁት ዑዛ እጁን ዘርግቶ የቃል ኪዳኑ ታቦት እንዳይወድቅ ደገፈ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ናኮንም አውድማ ደረሱ፤ ዖዛም በሬዎቹ አነቃንቀዋት ነበርና ይይዛት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ታቦት እጁን ዘረጋ፤ አስተካከላትም። ሲይዛትም በሬው ወጋው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ናኮንም አውድማ በደረሱ ጊዜ በሬዎቹ ይፋንኑ ነበርና ዖዛ እጁን ዘርግቶ የእግዚአብሔርን ታቦት ያዘ። |
እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አጣድ ከተባለው ዐውድማ ሲደርሱ፣ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ምርር ብለው አለቀሱ፤ ዮሴፍም በዚያ ለአባቱ ሰባት ቀን ልቅሶ ተቀመጠ።
“አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና ዕቃዎቹን፣ ንዋየ ቅድሳቱንም በሙሉ ሸፍነው ከጨረሱ በኋላ ሰፈሩ ለመንቀሳቀስ ዝግጁ ሲሆን፣ ቀዓታውያን ለመሸከም ይምጡ፤ እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን መንካት የለባቸውም፤ ስለዚህ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያሉትን እነዚህን ዕቃዎች የሚሸከሙ ቀዓታውያን ናቸው።