2 ሳሙኤል 6:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም የበፍታ ኤፉድ በወገቡ ታጥቆ በሙሉ ኀይሉ በእግዚአብሔር ፊት ይጨፍር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም የበፍታ ኤፉድ በወገቡ ታጥቆ በሙሉ ኀይሉ በጌታ ፊት ይጨፍር ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት ከበፍታ የተሠራ ሽርጥ በወገቡ ዙሪያ ታጥቆ እግዚአብሔርን በማክበር በሙሉ ኀይሉ ያሸበሽብ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በእግዚአብሔር ፊት በገና ይደረድር ነበር፤ ዳዊትም ለዐይን የሚያንጸባርቅ የሐር ቀሚስ ለብሶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በሙሉ ኃይሉ በእግዚአብሔር ፊት ይዘፍን ነበር፥ ዳዊትም የበፍታ ኤፉድ ለብሶ ነበር። |
ዳዊት ቤተ ሰቡን ለመመረቅ ወደ ቤቱ በተመለሰ ጊዜ፣ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ልትቀበለው ወጥታ፣ “ዛሬ የእስራኤል ንጉሥ በመኳንንቱ ገረዶች ፊት እንደ አንድ ተራ ሰው ዕራቍቱን መታየቱ ክብሩ ሆኖ ነው!” አለችው።
ታቦቱን የተሸከሙት ሌዋውያን ሁሉ፣ መዘምራኑና የመዘምራኑ አለቃ ክናንያ የለበሱትን ዐይነት ከቀጭን በፍታ የተሠራ ልብስ ዳዊትም ለብሶ ነበር፤ እንዲሁም ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ ለብሶ ነበር።
ዮፍታሔ ምጽጳ ወዳለው ቤቱ ተመለሰ። እነሆ፤ ልጁ አታሞ እየደለቀች በመዝፈን ልትቀበለው ወጣች፤ እርሷም አንዲት ልጁ ብቻ ነበረች፤ ከርሷ በቀር ወንድም ሆነ ሴት ልጅ አልነበረውም።
አድፍጣችሁ ተጠባበቁ። የሴሎ ልጃገረዶች ለጭፈራ ወደዚያ በሚወጡበት ጊዜ፣ ከወይኑ አትክልት ቦታ ወጥታችሁ ከልጃገረዶቹ ለየራሳችሁ ሚስት ጥለፉ፤ ወደ ብንያምም ምድር ሂዱ።
የእኔ ካህን እንዲሆን፣ ወደ መሠዊያዬ እንዲወጣ፣ ዕጣን እንዲያጥን፣ በፊቴም ኤፉድ እንዲለብስ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ አባትህን መረጥሁት። ደግሞም እስራኤላውያን በእሳት የሚያቀርቡትን ቍርባን ሁሉ ለአባትህ ቤት ሰጠሁ።
ንጉሡም ዶይቅን፣ “እንግዲያውስ አንተው ዙርና ካህናቱን ግደላቸው” ብሎ አዘዘው። ኤዶማዊው ዶይቅም ዞረና ገደላቸው። በዚያች ዕለት ሰማንያ ዐምስት የበፍታ ኤፉድ የለበሱ ካህናትን ገደለ።