2 ሳሙኤል 4:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ቤቱ ውስጥ የገቡት ኢያቡስቴ በመኝታ ክፍሉ ውስጥ ተኝቶ ሳለ ነበር፤ ወግተው ከገደሉትም በኋላ ራሱን ቈርጠው በመውሰድ፣ ሌሊቱን ሁሉ በዓረባ መንገድ ተጓዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ቤቱ ውስጥ የገቡት ኢያቡስቴ በመኝታ ክፍሉ ውስጥ ተኝቶ ሳለ ነበር፤ ወግተው ከገደሉትም በኋላ ራሱን ቆርጠው በመውሰድ፥ ሌሊቱን ሁሉ በዓራባ መንገድ ተጓዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከገቡም በኋላ ወደ ኢያቡስቴ መኝታ ክፍል ዘለቁ፤ እርሱም በአልጋ ላይ ተኝቶ ሳለ ወግተው ገደሉት፤ ራሱንም ቈርጠው ወሰዱ፤ ሌሊቱንም ሁሉ በዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ በኩል አልፈው ሄዱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ኢያቡስቴ በእልፍኙ በምንጣፉ ላይ ተኝቶ ሳለ መቱት፥ ገደሉትም፤ ራሱንም ቈርጠው ወሰዱት፥ በዓረባም መንገድ ሌሊቱን ሁሉ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ እርሱ በእልፍኙ በምንጣፉ ላይ ተኝቶ ሳለ መቱት፥ ገደሉትም፥ ራሱንም ቆርጠው ወሰዱት፥ በዓረባም መንገድ ሌሊቱን ሁሉ ሄዱ። |
አባይ በጓጕንቸሮች ይሞላል፤ ወጥተውም ወደ ቤተ መንግሥትህና ወደ መኝታ ክፍልህ፣ ወደ ዐልጋህም ወደ ሹማምቶችህና ወደ ሕዝብህ ቤቶች፣ ወደ ምድጆችህና ወደ ቡሖቃዎችህ ይገባሉ።
ዳዊት ሮጦ በላዩ ላይ ቆመ፤ ከዚያም የፍልስጥኤማዊውን ሰይፍ ከሰገባው መዝዞ አወጣው፤ እርሱንም ከገደለው በኋላ ራሱን በሰይፍ ቈረጠው። ፍልስጥኤማውያንም ጀግናቸው መሞቱን ባዩ ጊዜ ሸሹ።
ከዚያም የሳኦልን ራስ ቈርጠው፣ የጦር መሣሪያውንም ገፍፈው፣ ለቤተ ጣዖቶቻቸውና ለሕዝቡ የምሥራቹን እንዲናገሩ ወደ መላው የፍልስጥኤም ምድር መልክተኞችን ላኩ።