ንጉሥ ዳዊት በራሱና በሳኦል ልጅ በዮናታን መካከል በእግዚአብሔር ፊት ስላደረጉት መሐላ ሲል የሳኦልን ልጅ፣ የዮናታንን ልጅ ሜምፊቦስቴን ከሞት አተረፈ።
2 ሳሙኤል 4:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳኦል ልጅ ዮናታን ሁለት እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ ልጅ ነበረው። እርሱም የሳኦልና የዮናታን አሟሟት ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የዐምስት ዓመት ልጅ ነበረ። ሽባ የሆነውንም በዚህ ጊዜ ሞግዚቱ አንሥታው በጥድፊያ ስትሸሽ በመውደቁ ነው። ስሙም ሜምፊቦስቴ ይባል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳኦል ልጅ ዮናታን ሁለት እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ ልጅ ነበረው። እርሱም የሳኦልና የዮናታን አሟሟት ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ። ሽባ የሆነውንም በዚህ ጊዜ ሞግዚቱ አንሥታው በጥድፊያ ስትሸሽ በመውደቁ ነው። ስሙም መፊቦሼት ይባል ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌላው የሳኦል ዘር የዮናታን ልጅ መፊቦሼት ሲሆን፥ እርሱ ሳኦልና ዮናታን በተገደሉ ጊዜ ገና የአምስት ዓመት ልጅ ነበር፤ የእነርሱን ሞት የሚገልጠው ወሬ ከኢይዝራኤል ከተማ በተነገረ ጊዜ ሞግዚቱ እርሱን ይዛ ሸሸች፤ ነገር ግን በጥድፍያ በምትሸሽበት ጊዜ ከእጅዋ ወደቀ፤ ከዚህም የተነሣ ሽባ ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሳኦልም ልጅ ለዮናታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበረው። የሳኦልና የዮናታን ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ፤ ሞግዚቱም አዝላው ሸሸች፤ ልትሸሽም ስትሮጥ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜምፌቡስቴ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሳኦልም ልጅ ለዮናታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበረው። የሳኦልና የዮናታን ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ፥ ሞግዚቱም አዝላው ሸሸች፥ ፈጥናም ስትሸሽ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜምፊቦስቴ ነበረ። |
ንጉሥ ዳዊት በራሱና በሳኦል ልጅ በዮናታን መካከል በእግዚአብሔር ፊት ስላደረጉት መሐላ ሲል የሳኦልን ልጅ፣ የዮናታንን ልጅ ሜምፊቦስቴን ከሞት አተረፈ።
ንጉሡም፣ “የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዳደርግለት ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው የለምን?” ሲል ጠየቀው። ሲባም ለንጉሡ፣ “እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮናታን ልጅ አለ” ብሎ መለሰለት።
የሳኦል ልጅ፣ የዮናታን ልጅ ሜምፊቦስቴ ወደ ዳዊት በመጣ ጊዜ፣ አክብሮቱን ለመግለጥ ለጥ ብሎ እጅ ነሣ። ዳዊትም፣ “ሜምፊቦስቴ” ብሎ ጠራው። እርሱም፣ “እነሆ፤ አገልጋይህ” አለ።