የሳኦል ልጅ ዮናታን ሁለት እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ ልጅ ነበረው። እርሱም የሳኦልና የዮናታን አሟሟት ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የዐምስት ዓመት ልጅ ነበረ። ሽባ የሆነውንም በዚህ ጊዜ ሞግዚቱ አንሥታው በጥድፊያ ስትሸሽ በመውደቁ ነው። ስሙም ሜምፊቦስቴ ይባል ነበር።
2 ሳሙኤል 4:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የብኤሮት ሕዝብ ወደ ጊቴም በመሸሽ እስከ ዛሬም በመጻተኛነት እዚያው ይኖራልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የበኤሮት ሕዝብ ወደ ጊታይም በመሸሽ እስከ ዛሬም በመጻተኝነት እዚያው ይኖራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የበኤሮት የመጀመሪያዎቹ ነዋሪዎችም ወደ ጊታይም ተሰደው ከዚያን ዘመን ጀምሮ የሚኖሩት በዚያው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤሮታውያንም ወደ ጌቴም ሸሽተው ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ተጠግተው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብኤሮታውያንም ወደ ጌቴም ሸሽተው ነበር፥ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ተጠግተው ነበር። |
የሳኦል ልጅ ዮናታን ሁለት እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ ልጅ ነበረው። እርሱም የሳኦልና የዮናታን አሟሟት ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የዐምስት ዓመት ልጅ ነበረ። ሽባ የሆነውንም በዚህ ጊዜ ሞግዚቱ አንሥታው በጥድፊያ ስትሸሽ በመውደቁ ነው። ስሙም ሜምፊቦስቴ ይባል ነበር።
በሸለቆው ማዶና ከዮርዳኖስ ባሻገር ያሉ እስራኤላውያን፣ የእስራኤል ሰራዊት መሸሹን፣ ሳኦልና ልጆቹም መሞታቸውን ሲያዩ፣ ከተሞቻቸውን ለቅቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው።