2 ሳሙኤል 3:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳኦል ቤትና የዳዊት ቤት በጦርነት ላይ በነበሩበት ጊዜ፣ አበኔር በሳኦል ቤት ላይ ኀይሉን ያጠናክር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳኦል ቤትና የዳዊት ቤት በጦርነት ላይ በነበሩበት ጊዜ፥ አበኔር በሳኦል ቤት ሆኖ ኀይሉን ያጠናክር ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሳኦል ቤተሰብና በዳዊት ቤተሰብ መካከል ጦርነቱ እየቀጠለ በሄደ መጠን አበኔር በሳኦል ቤተሰብ እየበረታ ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሳኦል ቤትና በዳዊት ቤት መካከል ጦርነት ሆኖ ሳለ አበኔር የሳኦልን ቤት ያበረታ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሳኦል ቤትና በዳዊት ቤት መካከል ጦርነት ሆኖ ሳለ አበኔር በሳኦል ቤት ይበረታ ነበር። |
ከዚያም ኢዩ ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ ጋራ ወደ በኣል ቤተ ጣዖት ገባ። የበኣልንም አገልጋዮች፣ “እንግዲህ የበኣል አገልጋዮች ብቻ እንጂ የእግዚአብሔር አገልጋዮች እዚህ ዐብረዋችሁ አለመኖራቸውን አረጋግጡ” አላቸው።
ሄደህ፣ ጦርነቱን በቈራጥነት ብትዋጋም እንኳ፣ የመርዳትና የመጣል ኀይል ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለ ሆነ፣ እግዚአብሔር በጠላቶችህ ፊት ይጥልሃል።”