2 ሳሙኤል 3:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ኢያቡስቴ መልክተኛ ልኮ፣ ሜልኮልን ከባሏ ከሌሳ ልጅ ከፈልጢኤል ወሰዳት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያቡስቴም መልክተኛ ልኮ፥ ሜልኮልን ከባሏ ከላይሽ ልጅ ከፓልጢኤል ወሰዳት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ኢያቡስቴ መልእክተኛ በመላክ ሜልኮል የላዊሽ ልጅ ከሆነው ከባልዋ ከፓልጢኤል ልጅ አስወሰዳት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያቡስቴም ልኮ ከሴሊስ ልጅ ከባልዋ ከፈላጥያል ወሰዳት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያቡስቴም ልኮ ከሌሳ ልጅ ከባልዋ ከፈልጢኤል ወሰዳት። |
ከዚያም ዳዊት፣ “የመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ማጫ የከፈልሁባትን ሚስቴን ሜልኮልን ስጠኝ” ብሎ ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ መልክተኞች ላከበት።
ባሏም እስከ ባሑሪም ከተማ ድረስ እያለቀሰ ተከትሏት ሄደ፤ ከዚያም አበኔር፣ “በል ይበቃል! ወደ ቤትህ ተመለስ” አለው። ስለዚህም ተመለሰ።