La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 24:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ደግሞም ወደ ጢሮስ ምሽግ፣ ወደ ኤዊያውያንና ወደ ከነዓናውያን ከተሞች፣ በመጨረሻም በይሁዳ ደቡብ ወዳለችው ወደ ቤርሳቤህ ሄዱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያ ወደ ጢሮስ ምሽግ፥ ወደ ሒዋውያንና ወደ ከነዓናውያን ከተሞች፥ በይሁዳ ደቡብ ወዳለችው ወደ ቤርሳቤህ ሄዱ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቀጥሎም በደቡብ በኩል ወደተመሸገችው ወደ ጢሮስ ከተማና እንዲሁም ወደ ሒዋውያንና ወደ ከነዓናውያን ከተሞች ሁሉ ሄዱ፤ በመጨረሻም በይሁዳ ወደምትገኘው ወደ ቤርሳቤህ ዘለቁ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ጤሮ​ስም ምሽግ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ከተ​ሞች ሁሉ መጡ፤ በይ​ሁ​ዳም ደቡብ በኩል በቤ​ር​ሳ​ቤህ ወጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ጢሮስም ምሽግ ወደ ኤዊያውያንና ወደ ከነዓናውያንም ከተሞች ሁሉ መጡ፥ በይሁዳም ደቡብ በኩል በቤርሳቤህ ወጡ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 24:7
10 Referencias Cruzadas  

ስለዚህም ንጉሡ ኢዮአብንና ዐብረውት ያሉትን የጦር አዛዦች፣ “ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ወዳሉት የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ሂዱ፤ ብዛታቸው ምን ያህል እንደ ሆነ ለማወቅ እንድችልም ተዋጊዎቹን መዝግቡ” አላቸው።


ምድሪቱን ሁሉ ዞረው ከዘጠኝ ወር ከሃያ ቀን በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።


ጢሮስ ለራሷ ምሽግ ሠርታለች፤ ብሩን እንደ ዐፈር ወርቁንም እንደ መንገድ ላይ ትቢያ ቈልላለች።


ደግሞም በምሥራቅና በምዕራብ ወደሚገኙት ወደ ከነዓናውያን፣ ወደ አሞራውያን፣ ወደ ኬጢያውያን፣ ወደ ፌርዛውያንና በኰረብታማው አገር ወደሚኖሩት ወደ ኢያቡሳውያን፣ እንዲሁም ደግሞ በምጽጳ ምድር በአርሞንዔም ተራራ ግርጌ ወዳሉት ወደ ኤዊያውያን ነገሥታት መልእክት ላከ።


በመቀጠልም ወደ ዔብሮን፣ ወደ ረአብ፣ እንዲሁም ወደ ሐሞንና ወደ ቃና ሽቅብ ወጥቶ እስከ ታላቁ ሲዶና ይደርሳል።


ድንበሩ ወደ ራማ ከዞረ በኋላ ወደ ተመሸገው ወደ ጢሮስ ከተማ ታጥፎ ወደ ሖሳ ይመለስና በአክዚብ በኩል ሜድትራኒያን ባሕር ደርሶ ይቆማል፤


በዮርዳኖስ ምዕራብ ባለው በተራራማው አገር፣ በቈላማው ምድር እንዲሁም እስከ ሊባኖስ በሚደርሰው በመላው በታላቁ ባሕር ዳርቻ የነበሩት የኬጢያውያን፣ የአሞራውያን፣ የከነዓናውያን፣ የፌርዛውያን፣ የኤዊያውያን፣ የኢያቡሳውያን ነገሥታት ይህን በሰሙ ጊዜ፣


የእስራኤልም ሰዎች ለኤዊያውያኑ፣ “እናንተ የምትኖሩት እዚሁ ቅርብ ቢሆንስ? ታዲያ ከእናንተ ጋራ እንዴት ቃል ኪዳን እንገባለን?” አሏቸው።


እነዚህም አሕዛብ ዐምስቱ የፍልስጥኤም ገዦች፣ ከነዓናውያን በሙሉ፣ ሲዶናውያንና ከበኣል አርሞንዔም ተራራ እስከ ሐማት መግቢያ ባሉት የሊባኖስ ተራሮች የሚኖሩ ኤዊያውያን ነበሩ።