2 ሳሙኤል 24:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ወደ ገለዓድና ወደ ተባሶን አዳሰይ፣ ቀጥሎም ወደ ዳንየዓን ከዚያም ዞረው ወደ ሲዶና ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ወደ ገለዓድና በሒታውያን ግዛት ወዳለው ወደ ቃዴስ ዘለቁ፤ ከዚያም ወደ ዳን፥ ከዳንም ወደ ሲዶና ዞሩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥለውም ወደ ገለዓድና በሒታውያን ግዛት ውስጥ ወዳለው ወደ ቃዴስ ዘለቁ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ዳን፥ ከዳንም ወደ ምዕራብ ታጥፈው ወደ ሲዶና ሄዱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ገለዓድም አዳሳይ ወደምትባል ወደ ተባሶን ሀገርም መጡ፤ ወደ ዳኒዳንና ወደ ኡዳንም ደረሱ፤ ወደ ሲዶናም ዞሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ገለዓድም ወደ ተባሶን አዳሰይ አገር መጡ፥ ወደ ዳንየዓንም ደረሱ፥ ወደ ሲዶናም ዞሩ፥ |
እጅግ ብዙ የሆነ የቀንድ ከብት፣ የበግና የፍየል መንጋዎች የነበሯቸው የሮቤልና የጋድ ነገዶች የኢያዜርና የገለዓድ ምድር ለከብት ምቹ ስፍራዎች መሆናቸውን አዩ።
እግዚአብሔርም በእስራኤል እጅ አሳልፎ ስለ ሰጣቸው ድል አደረጓቸው። በታላቂቱ ሲዶና መንገድ መጨረሻ እስከ ማስሮን፣ በስተ ምሥራቅም እስከ ምጽጳ ሸለቆ ድረስ አሳደዷቸው፤ ከእነርሱም በሕይወት የተረፈ አንድም ሰው አልነበረም።
ነገር ግን የዳን ዘሮች ርስታቸው አልበቃቸውም፣ ወደ ሌሼም ወጥተው አደጋ በመጣል ያዟት፤ ሰዎቹንም በሰይፍ ስለት ፈጅተው ይዞታቸው አደረጓት፤ በዚያው ሰፈሩ፤ ስሟንም ለውጠው በአባታቸው ስም ዳን አሏት።