2 ሳሙኤል 24:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አለው፤ “ሂድና ዳዊትን፣ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሦስት ነገሮችን ለምርጫ አቅርቤልሃለሁ፤ በአንተ ላይ አደርግብህ ዘንድ አንዱን ምረጥ’ በለው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሂድና ዳዊትን፥ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፤ ሦስት ነገሮችን አቅርቤልሃለሁ፤ በአንተ ላይ እንዳደርግብህ አንዱን ምረጥ’ በለው” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሂድና ለዳዊት እንዲህ ብለህ ንገረው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሦስት ነገሮችን በፊትህ አኖራለሁ፤ አደርግብህ ዘንድ ከእነርሱ አንዱን ምረጥ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሂድ ለዳዊት፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሦስት ነገሮች በፊትህ አኖራለሁ፥ አደርግብህ ዘንድ ከእነርሱ አንዱን ምረጥ ብለህ ንገረው አለው። |
ስለዚህም ጋድ ወደ ዳዊት ሄዶ፣ “በምድርህ የሦስት ዓመት ራብ ይምጣብህ? ወይስ ጠላቶችህ እያሳደዱህ ሦስት ወር ትሸሽ? ወይስ ደግሞ በምድርህ ላይ የሦስት ቀን መቅሠፍት ይምጣ? እንግዲህ አሁን ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ ዐስበህበት ወስን” አለው።
የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቍጠር ጀመረ፤ ሆኖም አልፈጸመውም፤ መቈጠራቸው በእስራኤል ላይ ቍጣ ስላመጣ፣ የተቈጠረውም በንጉሡ ዳዊት መዝገብ አልገባም።
እኔ ከአንተ ጋራ ነኝ፤ አድንሃለሁም’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘በአሕዛብ መካከል በትኜሃለሁ፤ እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፤ አንተን ግን ሙሉ በሙሉ አላጠፋህም፤ በመጠኑ እቀጣሃለሁ እንጂ፣ ያለ ቅጣት አልተውህም።’
ይኸውም፣ እኔ ጠላት እንድሆንባቸውና ወደ ጠላቶቻቸው ምድር እንድሰድዳቸው ያደረገኝን ኀጢአት ቢናዘዙ፣ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድና ስለ ኀጢአታቸው የሚገባውን ቅጣት ቢቀበሉ፣
ምድሪቱ እነርሱ ለቅቀዋት ስለ ሄዱ ባዶ ትቀራለች፤ እነርሱ በሌሉበት ጊዜም ባድማ ሆና በሰንበቷ ትደሰታለች፤ ሕጌን በማቃለላቸውና ሥርዐቴን በመናቃቸው፣ የኀጢአታቸውን ቅጣት ይቀበላሉ።