2 ሳሙኤል 22:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአፍንጫው ጢስ ወጣ፤ ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤ ከውስጡም ፍሙ ጋለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአፍንጫው የቁጣ ጢስ ወጣ፤ ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤ ከእርሱ የሚንበለበል ፍም ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአፍንጫው የቊጣ ጢስ ወጣ፤ ከአፉም የሚባላ የእሳት ነበልባልና የሚያቃጥል ፍም ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቍጣው ጢስ ወጣ፤ ከአፉም የሚበላ እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእርሱ ተቃጠለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከቁጣው ጢስ ወጣ፥ ከአፉም የሚበላ እሳት ነደደ፥ ፍምም ከእርሱ በራ። |
የሲና ተራራ እግዚአብሔር በእሳት ስለ ወረደበት በጢስ ተሸፍኖ ነበር። ጢሱ ከምድጃ እንደሚወጣ ጢስ ወደ ላይ ተትጐለጐለ፤ ተራራውም በሙሉ በኀይል ተናወጠ።
እነሆ፤ የእግዚአብሔር ስም፣ ከሚነድድ ቍጣ፣ ጥቅጥቅ ካለና ከሚትጐለጐል የጢስ ደመና ጋራ ከሩቅ ይመጣል፤ ከንፈሮቹ ቍጣን የተሞሉ ናቸው፤ ምላሱም የሚባላ እሳት ነው።
ከቀድሞ ጀምሮ ቶፌት የተባለ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅቷል፤ ለንጉሡም ተበጅቷል፤ ማንደጃ ጕድጓዱም ሰፊና ጥልቅ ነው፤ በውስጡም ብዙ እሳትና ማገዶ አለ፤ የእግዚአብሔርም እስትንፋስ እንደ ፈሳሽ ድኝ ያቀጣጥለዋል።
ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፤ “ሕዝቡ ይህን ቃል ስለ ተናገረ፣ ቃሌን በአፍህ ውስጥ የሚፋጅ እሳት፣ ይህንም ሕዝብ ማገዶ አደርጋለሁ፤ እሳቱም ይበላቸዋል፤