2 ሳሙኤል 22:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከላይ እጁን ዘርግቶ ያዘኝ፤ ከጥልቅ ውሆችም ውስጥ አወጣኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከላይ እጁን ዘርግቶ ያዘኝ፤ ከጥልቅ ውሆችም ውስጥ አወጣኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከላይ ሆኖ እጁን በመዘርጋት ያዘኝ፤ ከጥልቅ ውሃም ስቦ አወጣኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከላይ ላከ፤ ወሰደኝም፤ ከብዙ ውኆችም አወጣኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከላይ ሰደደ፥ ወሰደኝም፥ ከብዙ ውኆችም አወጣኝ። |
በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ፣ ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤ ወንዙን ስትሻገረው፣ አያሰጥምህም፤ በእሳት ውስጥ ስትሄድ፣ አያቃጥልህም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።