ሄዶ የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን ዐፅም ከኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ወሰደ፤ የኢያቢስ ገዦች፣ ፍልስጥኤማውያን ሳኦልን በጊልቦዓ ከገደሉ በኋላ እነርሱን ከሰቀሉት ከቤትሳን አደባባይ በድብቅ ወስደዋቸው ነበር።
2 ሳሙኤል 21:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን ዐፅም ከዚያ አመጣ፤ እንዲሁም የእነዚያን የተገደሉትን ሰዎች ዐፅም ሰበሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን ዐፅም ከዚያ አምጥቶ፥ የእነዚያን የተሰቀሉትን ሰዎች ዐፅምም ሰበሰቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት የሳኦልንና የዮናታንን ዐፅም ወሰደ፤ እንዲሁም ተሰቅለው የነበሩትን የሰባቱን ሰዎች አስከሬን ሰበሰበ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም የሳኦልን አጥንትና የልጁን የዮናታንን አጥንት አመጣ፤ የተሰቀሉትንም ሰዎች አጥንት ሰበሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት ይዞ መጣ፥ የተሰቀሉትንም ሰዎች አጥንት ሰበሰቡ። |
ሄዶ የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን ዐፅም ከኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ወሰደ፤ የኢያቢስ ገዦች፣ ፍልስጥኤማውያን ሳኦልን በጊልቦዓ ከገደሉ በኋላ እነርሱን ከሰቀሉት ከቤትሳን አደባባይ በድብቅ ወስደዋቸው ነበር።
የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን ዐፅም በብንያም አገር ጼላ በተባለ ስፍራ በሳኦል አባት በቂስ መቃብር ቀበሩት፤ ንጉሡ ያዘዘውንም ሁሉ አደረጉ። ከዚያ በኋላም ስለ ምድሪቱ የቀረበውን ጸሎት እግዚአብሔር ሰማ።