2 ሳሙኤል 20:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የኢዮአብ ሰዎች፣ ከሊታውያን፣ ፈሊታውያን እንዲሁም ሌሎች ኀያላን ጦረኞች በሙሉ በአቢሳ አዛዥነት ወጡ፤ ከኢየሩሳሌም የወጡትም የቢክሪ ልጅ ሳቤዔን ለማሳደድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቢሳንም ተከትለው የኢዮአብ ሰዎች ከሊታውያን፥ ፈሊታውያን፥ እንዲሁም ሌሎች ኀያላን ጦረኞች በሙሉ ወጡ፤ የቢክሪ ልጅ ሼባዕን ለማሳደድ ከኢየሩሳሌም ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የኢዮአብ ወታደሮች፥ የንጉሡ የክብር ዘበኞችና ሌሎች ወታደሮችም ከአቢሳ ጋር ከኢየሩሳሌም ወጥተው የቢክሪን ልጅ ሼባዕን በመከታተል አሳደዱት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቢሳና የኢዮአብ ሰዎች ከሊታውያንም፥ ፈሊታውያንም፥ ኀያላኑም ሁሉ ወጥተው ተከተሉት፤ ከኢየሩሳሌምም ወጥተው የቢኮሪ ልጅ ሳቡሄን አሳደዱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቢሳንም ተከትለው የኢዮአብ ሰዎች ከሊታውያንም ፈሊታው ያንም ኃያላንም ሁሉ ሄዱ፥ የቢክሪንም ልጅ ሳቤዔን ለማሳደድ ከኢየሩሳሌም ወጡ። |
ንጉሡ እንዲህ አላቸው፤ “የጌታችሁን አገልጋዮች ይዛችሁ በመሄድ ልጄን ሰሎሞንን በራሴ በቅሎ ላይ አስቀምጡት፤ ወደ ግዮንም ይዛችሁት ውረዱ።
ስለዚህ ካህኑ ሳዶቅ፣ ነቢዩ ናታን፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ ከሊታውያንና ፈሊታውያን ወርደው ሰሎሞንን በንጉሥ ዳዊት በቅሎ አስቀምጠው በማጀብ ወደ ግዮን አመጡት።
ንጉሡ ካህኑ ሳዶቅ፣ ነቢዩ ናታን፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ ከሊታውያንና ፈሊታውያን ዐብረውት እንዲሄዱ አድርጓል፤ እነርሱም በንጉሡ በቅሎ አስቀመጡት።