ሳቤዔም በእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል ዐልፎ ወደ አቤል ቤትማዓካና ወደ መላው የቢክሪያውያን ግዛት መጣ፤ የቢክሪ ሰዎችም ተሰብስበው ተከተሉት።
2 ሳሙኤል 20:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኢዮአብ ጋራ ያለውም ሰራዊት መጥቶ፣ ሳቤዔን በአቤል ቤትመዓካ በኩል ከበበው፤ በስተ ውጭም እስከ ከተማዪቱ ግንብ ጫፍ ድረስ ዙሪያውን የዐፈር ድልድል ሠሩ፤ ግንቡን ለመናድ በኀይል በሚደበድቡበት ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኢዮአብ ጋር ያለውም ሠራዊት መጥቶ ሼባዕን በአቤል ቤት መዓካ በኩል ከበበው፤ በስተ ውጭም እስከ ከተማዪቱ ግንብ ጫፍ ድረስ ዙሪያውን የዐፈር ድልድል ሠሩ፤ ግንቡን ለመናድ በኃይል ይደበድቡት ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢዮአብ ወታደሮች ሼባዕ እዚያ መሆኑን ስለ ሰሙ ሄደው ከተማይቱን ከበቡ፤ በስተውጪ በኩል ቅጽሩን አስደግፈው የዐፈር ቊልል ሠሩ፤ ቀጥሎም ቅጽሩ እንዲወድቅ ከስሩ መቈፈር ጀመሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤተ ማካና በአቤልም መጥተው ከበቡት፤ በከተማዪቱም ላይ እስከ ቅጥርዋ ድረስ የአፈርን ድልድል ደለደሉ፤ እነርሱም ከአጥሩ ቀጥሎ ቆሙ፤ ቅጥሩንም ያፈርሱ ዘንድ ከኢዮአብ ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ተስማሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤትመዓካ ባለ በአቤልም መጥተው ከበቡት፥ በከተማይቱም ላይ እስከ ቅጥርዋ ድረስ የአፈርን ድልድል ደለደሉ፥ ቅጥሩንም ያፈርሱ ዘንድ ከኢዮአብ ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ይደባደቡ ነበር። |
ሳቤዔም በእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል ዐልፎ ወደ አቤል ቤትማዓካና ወደ መላው የቢክሪያውያን ግዛት መጣ፤ የቢክሪ ሰዎችም ተሰብስበው ተከተሉት።
ቤን ሃዳድም የንጉሥ አሳን ሐሳብ ተቀብሎ፣ የጦር አዛዦቹን በእስራኤል ከተሞች ላይ አዘመተ፤ እርሱም ዒዮንን፣ ዳንን፣ አቤል ቤት ማዕካን እንዲሁም ንፍታሌምን ጨምሮ ኪኔሬትን በሙሉ ድል አድርጎ ያዘ።
በእስራኤል ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን፣ የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጥቶ ዒዮን፣ አቤልቤትመዓካን፣ ያኖዋን፣ ቃዴስንና አሦርን፣ ገለዓድንና ገሊላን፣ የንፍታሌምንም ምድር ጭምር ያዘ፤ ሕዝቡንም ማርኮ ወደ አሦር ወሰደው።
“ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፤ “ ‘ወደዚህች ከተማ ፈጽሞ አይገባም፤ ፍላጻም አይወረውርባትም፤ ጋሻ አንግቦ አይቀርብም፤ በዐፈርም ቍልል አይከብባትም።
“ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፤ “ወደዚህች ከተማ ፈጽሞ አይገባም፤ ፍላጻም አይወረውርባትም፤ ጋሻ አንግቦ አይቀርብም፤ በዐፈርም ቍልል አይከብባትም።
“እነሆ፤ ከተማዪቱን ለመያዝ የዐፈር ድልድል በዙሪያዋ ተሠርቷል፤ ከሰይፍ፣ ከራብና ከቸነፈር የተነሣ ከተማዪቱን ለሚወጓት ለባቢሎናውያን ዐልፋ ልትሰጥ ነው፤ እንደምታየውም የተናገርኸው እየተፈጸመ ነው።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከባቢሎናውያን ጋራ ባለው ውጊያ፣ ዐፈር በመደልደልና በሰይፍ የሚደረገውን ጥቃት ለመከላከል ስለ ፈረሱት ስለዚህች ከተማ ቤቶችና ስለ ይሁዳ ነገሥታት ቤተ መንግሥት እንዲህ ይላል፤
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “ዛፎቹን ቍረጡ፤ በኢየሩሳሌም ዙሪያ የዐፈር ድልድል ሥሩ። ይህች ከተማ ቅጣት ይገባታል፤ ግፍን ተሞልታለችና።
ከዚያም በወታደር እንደሚከበብ ክበባት፤ ምሽግ ሥራባት፤ ዐፈር ደልድልባት፤ ጦር ሰፈሮችን ቀብቅብባት፤ ቅጥር መደርመሻ ግንዶችንም በዙሪያዋ አስቀምጥባት።