ሳኦልና ዮናታን በሕይወት እያሉ፣ የሚዋደዱና የሚስማሙ ነበሩ፤ ሲሞቱም አልተለያዩም፤ ከንስርም ይልቅ ፈጣኖች፣ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ።
2 ሳሙኤል 2:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሦስቱ የጽሩያ ወንዶች ልጆች ኢዮአብ፣ አቢሳና አሣሄል እዚያው ነበሩ። አሣሄል እንደ ዱር ሚዳቋ በሩጫ ፈጣን ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሦስቱ የጽሩያ ልጆች ኢዮአብ፥ አቢሳና አሣሄል እዚያው ነበሩ። አሣሄል እንደ ዱር ሚዳቋ በሩጫ ፈጣን ነበረ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብ፥ አቢሳ፥ ዐሣሄል ተብለው የሚጠሩት ሦስቱም የጸሩያ ልጆች እዚያ ነበሩ፤ በሩጫ እንደ በረሓ ሚዳቋ ፈጣን የነበረው አሳሔል፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ሦስቱ የሦርህያ ልጆች ኢዮአብና አቢሳ፥ አሣሄልም ነበሩ፤ የአሣሄልም እግሮቹ ፈጣኖች ነበሩ፤ እንደ ዱር ሚዳቋም ሯጭ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ሦስቱ የጽሩያ ልጆች ኢዮአብና አቢሳ አሣሄልም ነበሩ፥ አሣሄልም እንደ ዱር ሚዳቋ በሩጫ ፈጣን ነበረ። |
ሳኦልና ዮናታን በሕይወት እያሉ፣ የሚዋደዱና የሚስማሙ ነበሩ፤ ሲሞቱም አልተለያዩም፤ ከንስርም ይልቅ ፈጣኖች፣ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ።
“የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ በእኔ ላይ ያደረገውን፣ እንዲሁም በእስራኤል ሰራዊት አዛዦች በኔር ልጅ በአበኔርና በዬቴር ልጅ በአሜሳይ ላይ የፈጸመውን አንተው ራስህ ታውቃለህ፤ ጦርነት ሳይኖር በሰላሙ ጊዜ ደማቸውን አፍስሷል፤ በዚህም ደም ወገቡ ላይ የታጠቀውን ቀበቶና በእግሩ ላይ ያደረገውን ጫማ በክሏል።
ዳዊት በምድረ በዳ በሚገኘው ምሽጉ ውስጥ ሳለ፣ ከጋድ ነገድ የሆኑ ሰዎች መጥተው የርሱን ሰራዊት ተቀላቀሉ፤ እነርሱም ለውጊያ የተዘጋጁ ጋሻና ጦር ለመያዝ የሚችሉ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ ፊታቸው እንደ አንበሳ ፊት የሚያስፈራና በየተራራውም ላይ እንደሚዘልል ሚዳቋ ፈጣኖች ነበሩ።
በአራተኛው ወር፣ አራተኛው የበላይ አዛዥ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል ሲሆን፣ በእግሩ የተተካውም ልጁ ዝባድያ ነው፤ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
ሌላም ነገር ከፀሓይ በታች አየሁ፤ ሩጫ ለፈጣኖች፣ ውጊያም ለኀያላን አይደለም፤ እንጀራ ለጥበበኞች፣ ወይም ባለጠግነት ለብልኆች፣ ወይም ሞገስ ለዐዋቂዎች አይሆንም፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።
ጌታ እግዚአብሔር ኀይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል። ለመዘምራን አለቃ፣ በባለአውታር መሣሪያዎቼ የተዘመረ መዝሙር።
ዳዊትም ኬጢያዊውን አቢሜሌክንና የጽሩያን ልጅ የኢዮአብን ወንድም አቢሳን፣ “ወደ ሳኦል ሰፈር ዐብሮኝ የሚወርድ ማነው?” ሲል ጠየቃቸው። አቢሳም፣ “እኔ ዐብሬህ እወርዳለሁ” አለ።