ከዚያም አበኔር፣ ኢዮአብን፣ “ከእናንተም ከእኛም ጕልማሶች ይነሡና በፊታችን በጨበጣ ውጊያ ይጋጠሙ” አለው። ኢዮአብም፣ “ይሁን ዕሺ ይጋጠሙ” ብሎ መለሰ።
2 ሳሙኤል 2:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዚያን ዕለቱ ጦርነት እጅግ ከባድ ነበር፤ አበኔርና የእስራኤል ሰዎች በዳዊት ሰዎች ድል ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዚያን ዕለት ፍልሚያ እጅግ መራር ነበር፤ በዳዊትም አገልጋዮች ፊት አበኔርና የእስራኤል ሰዎች ተሸነፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ቀን ከባድ ጦርነት ተደርጎ አበኔርና እስራኤላውያን በዳዊት ሰዎች ድል ተመቱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን እጅግ ጽኑ ሰልፍ ሆነ፤ በዳዊትም ሰዎች ፊት አበኔርና የእስራኤል ሰዎች ተሸነፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ጽኑ ሰልፍ ሆነ፥ በዳዊትም ባሪያዎች ፊት አበኔርና የእስራኤል ሰዎች ተሸነፉ። |
ከዚያም አበኔር፣ ኢዮአብን፣ “ከእናንተም ከእኛም ጕልማሶች ይነሡና በፊታችን በጨበጣ ውጊያ ይጋጠሙ” አለው። ኢዮአብም፣ “ይሁን ዕሺ ይጋጠሙ” ብሎ መለሰ።
ከዚያም እያንዳንዱ ሰው የባላጋራውን ራስ በመያዝ ሰይፉን በጐኑ እየሻጠበት ተያይዘው ወደቁ። ስለዚህም በገባዖን የሚገኘው ያ ቦታ “የሰይፍ ምድር” ተባለ።