የአቤሴሎምም አገልጋዮች ጌታቸው ያዘዛቸውን በአምኖን ላይ ፈጸሙ። ከዚያም የንጉሡ ልጆች በሙሉ ተነሥተው በየበቅሎዎቻቸው ላይ ተቀምጠው ሸሹ።
2 ሳሙኤል 18:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ አቤሴሎም ከዳዊት ሰዎች ጋራ ድንገት ተገናኘ፤ አቤሴሎም በበቅሎ ተቀምጦ ይሄድ ስለ ነበር፣ በቅሎዋ ጥቅጥቅ ያለ ቅርንጫፍ ባለው ትልቅ ወርካ ሥር በምታልፍበት ጊዜ፣ የአቤሴሎም ራስ በዛፉ ቅርንጫፍ ተያዘ፤ የተቀመጠበትም በቅሎ በሥሩ ስታልፍ፣ እርሱ በሰማይና በምድር መካከል ተንጠልጥሎ ቀረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ አቤሴሎም ከዳዊት ሰዎች ጋር ድንገት ተገናኘ፤ አቤሴሎም በበቅሎ ተቀምጦ ይሄድ ስለ ነበር፥ በቅሎዋ ጥቅጥቅ ያለ ቅርንጫፍ ባለው ትልቅ ባሉጥ ሥር በምታልፍበት ጊዜ፥ የአቤሴሎም ራስ በባሉጡ ቅርንጫፍ ተያዘ፤ የተቀመጠበትም በቅሎ በሥሩ ስታልፍ፥ እርሱ በሰማይና በምድር መካከል ተንጠልጥሎ ቀረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በድንገት፥ አቤሴሎም ከዳዊት ተከታዮች ጥቂቱን አገኘ፤ አቤሴሎም በዚያን ጊዜ በበቅሎ ላይ ተቀምጦ ይጋልብ ስለ ነበር በቅሎዋ በአንድ ትልቅ የወርካ ዛፍ ሥር ስታልፍ ሳለ የዛፉ ቅርንጫፍ የአቤሴሎምን ራስ ጠጒር ያዘበት፤ በቅሎዋም በእግሮቹ መኻል ሾልካ ስትሄድ አቤሴሎም በዐየር ላይ ተንጠልጥሎ ቀረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሴሎምም ከዳዊት አገልጋዮች ጋር ተገናኘ፤ አቤሴሎምም በበቅሎ ተቀምጦ ነበር፤ በቅሎውም ብዙ ቅርንጫፍ ባለው በታላቅ ዛፍ በታች ገባ፤ ራሱም በዛፉ ተያዘ፤ በሰማይና በምድርም መካከል ተንጠለጠለ፤ ተቀምጦበትም የነበረው በቅሎ በበታቹ አለፈ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሴሎም ከዳዊት ባሪያዎች ጋር በድንገት ተገናኘ፥ አቤሴሎምም በበቅሎ ተቀምጦ ነበር፥ በቅሎውም ብዙ ቅርንጫፍ ባለው በታላቅ ዛፍ በታች ገባ፥ ራሱም በዛፉ ተያዘ፥ በሰማይና በምድር መካከል ተንጠለጠለ፥ ተቀምጦበትም የነበረ በቅሎ አለፈ። |
የአቤሴሎምም አገልጋዮች ጌታቸው ያዘዛቸውን በአምኖን ላይ ፈጸሙ። ከዚያም የንጉሡ ልጆች በሙሉ ተነሥተው በየበቅሎዎቻቸው ላይ ተቀምጠው ሸሹ።
የራስ ጠጕሩ ሲከብደው በዓመት አንድ ጊዜ ይቈርጠው ነበር፤ የተቈረጠውን በሚመዝነው ጊዜ ክብደቱ በንጉሥ ሚዛን ሁለት መቶ ሰቅል ይሆን ነበር።
አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተከተሉት ባየ ጊዜ፣ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወደሚገኝበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም መልክ መልክ ካስያዘ በኋላ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ። በዚህ ሁኔታም ሞቶ በአባቱ መቃብር ተቀበረ።
ኢዮአብም፣ “ከእንግዲህ በዚህ ሁኔታ ከአንተ ጋራ ጊዜ ማጥፋት አልችልም” አለው፤ ስለዚህ በእጁ ሦስት ጦር ይዞ ሄደና አቤሴሎም እዛፉ ላይ ተንጠልጥሎ ገና በሕይወት እያለ፣ ወርውሮ በልቡ ላይ ተከላቸው።
“ከሽብር የሚሸሽ ሁሉ፣ ጕድጓድ ውስጥ ይገባል፤ ከጕድጓዱም የሚወጣ፣ በወጥመድ ይያዛል፤ በሞዓብ ላይ፣ የቅጣቱን ዓመት አመጣለሁና፣” ይላል እግዚአብሔር።
በድኑን በዕንጨት ላይ እንደ ተሰቀለ አታሳድረው፤ ምክንያቱም በዕንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና፤ አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር እንዳታረክስ፣ በዚያ ዕለት ቅበረው።