Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 18:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ውጊያው በገጠሩ ሁሉ ተስፋፋ፤ በዚያ ቀን ሰይፍ ከጨረሰው ይልቅ ጫካ ውጦ ያስቀረው ሰው በለጠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ውጊያው በአገሩ ሁሉ ተስፋፋ፤ በዚያን ቀን ሰይፍ ከጨረሰው ይልቅ ጫካ ውጦ ያስቀረው ሰው በለጠ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ጦርነቱም በየገጠሩ ስለ ተስፋፋ በጦርነት ከሞቱት ሰዎች ይልቅ በደን ውስጥ ያለቁት ቊጥራቸው በዛ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከዚ​ያም ጦሩ በሀ​ገሩ ሁሉ ፊት ተበ​ተነ፤ በዚ​ያም ቀን በሰ​ይፍ ከተ​ገ​ደ​ሉት ሕዝብ ይልቅ በበ​ረሓ የሞቱ ይበ​ዛሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ከዚያም ሰልፉ በአገሩ ሁሉ ፊት ላይ ተበተነ፥ በዚያም ቀን ሰይፍ ከዋጠው ሕዝብ ይልቅ ዱር ብዙ ዋጠ።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 18:8
10 Referencias Cruzadas  

አንተ ግን እስትንፋስህን አነፈስህ፤ ባሕርም ከደናቸው፤ በኀያላን ውሆች፣ እንደ ብረት ሰጠሙ።


አምላክ ሆይ፤ ፍረድልኝ፤ ካልታመኑህ ሕዝብ ጋራ ተሟገትልኝ፤ ከአታላዮችና ከክፉዎች ሰዎችም አድነኝ።


እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ! አምላኬ ሆይ፤ ታደገኝ፤ የጠላቶቼን ሁሉ መንጋጋ ትመታለህ፤ የክፉዎችንም ጥርስ ትሰባብራለህ።


የቀሩት ወደ አፌቅ ከተማ ሸሹ፤ በዚያም በሃያ ሰባቱ ሺሕ ላይ ቅጥሩ ተንዶ ወደቀባቸው። ቤን ሃዳድም ወደ ከተማዪቱ ሸሽቶ በመሄድ ወደ አንዲት እልፍኝ ገብቶ ተደበቀ።


ከቤትሖሮን ወደ ዓዜቃ ቍልቍል በሚወስደው መንገድ ላይ፣ ከእስራኤላውያን ፊት በሚሸሹበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሰማይ ትልልቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸው፤ በእስራኤላውያን ሰይፍ ካለቁት ይልቅ በወረደው የበረዶ ድንጋይ ያለቁት በልጠው ተገኙ።


እዚያም የእስራኤል ሰራዊት በዳዊት ሰዎች ተመታ፤ በዚያም ቀን ታላቅ ዕልቂት ሆነ፤ ሃያ ሺሕም ሰው ተገደለ።


በዚህ ጊዜ አቤሴሎም ከዳዊት ሰዎች ጋራ ድንገት ተገናኘ፤ አቤሴሎም በበቅሎ ተቀምጦ ይሄድ ስለ ነበር፣ በቅሎዋ ጥቅጥቅ ያለ ቅርንጫፍ ባለው ትልቅ ወርካ ሥር በምታልፍበት ጊዜ፣ የአቤሴሎም ራስ በዛፉ ቅርንጫፍ ተያዘ፤ የተቀመጠበትም በቅሎ በሥሩ ስታልፍ፣ እርሱ በሰማይና በምድር መካከል ተንጠልጥሎ ቀረ።


ልጄ ሆይ፤ እግዚአብሔርንና ንጉሥን ፍራ፤ ከዐመፀኞችም ጋራ አትተባበር፤


ሁለቱም የሚያመጡት መዓት፤ ምን እንደሚሆን ማን ያውቃል?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios