2 ሳሙኤል 18:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢትዮጵያዊው ደርሶ፣ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ የምሥራች! ዛሬ እግዚአብሔር ከተነሡብህ ጠላቶችህ ሁሉ ታድጎሃል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ኢትዮጵያዊው ደርሶ፥ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ የምሥራች! ዛሬ ጌታ ከተነሡብህ ጠላቶችህ ሁሉ ታድጎሃል” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ኢትዮጵያዊው አገልጋይ እዚያ ደረሰና ንጉሡን “ንጉሥ ሆይ! የምሥራች ቃል ይዤልህ መጥቼአለሁ፤ በአንተ ላይ በዐመፅ የተነሣሡብህን ድል እንድታደርግ ዛሬ እግዚአብሔር ረድቶሃል!” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም፥ ኩሲ መጣ፤ ኩሲም፥ “እግዚአብሔር በላይህ የተነሡትን ሁሉ ዛሬ እንደ ተበቀለልህ ለጌታዬ ለንጉሡ ወሬ አምጥቻለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ ኵሲ መጣ፥ ኵሲም፦ እግዚአብሔር በላይህ የተነሡትን ሁሉ ዛሬ እንደ ተበቀለልህ ለጌታዬ ለንጉሡ ወሬ አምጥቼአለሁ አለ። |
አኪማአስም ጮኾ ንጉሡን፣ “ሁሉም ነገር ተሳክቷል” አለ፤ ከዚያም ወደ መሬት ለጥ ብሎ በንጉሡ ፊት እጅ ነሣና፣ “በጌታዬ በንጉሡ ላይ እጃቸውን ያነሡትን ሰዎች አሳልፎ የሰጠ አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!” አለ።
ከዚያም ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል ለጥቂት ጊዜ በጣም ታወከ፤ ሐሳቡም አስደነገጠው። ንጉሡም፣ “ብልጣሶር ሆይ፤ ሕልሙም ሆነ ትርጕሙ አያስደንግጥህ” አለው። ብልጣሶርም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “ሕልሙ ለሚጠሉህ ይሁን፤ ትርጕሙም ለጠላቶችህ!
“እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ ሁሉ ይጥፉ፤ አንተን የሚወድዱህ ግን፣ የንጋት ፀሓይ በኀይል እንደሚወጣ እንዲያ ይሁኑ።” ከዚያም በኋላ ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች።