ከዚያም ጠባቂው ሌላ ሰው ሲሮጥ አይቶ፣ ዘበኛውን ተጣራና፣ “እነሆ ሌላም ሰው ብቻውን እየሮጠ በመምጣት ላይ ነው!” አለ። ንጉሡም፣ “ይኸኛውም መልካም ወሬ ይዞ የመጣ መሆን አለበት” አለ።
2 ሳሙኤል 18:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠባቂውም፣ “የመጀመሪያው ሰው ሩጫ የሳዶቅን ልጅ የአኪማአስን ሩጫ ይመስለኛል” አለ። ንጉሡም፣ “እርሱማ ጥሩ ሰው ነው፤ የምሥራች ሳይዝ አይመጣም” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠባቂውም፥ “የመጀመሪያው ሰው ሩጫ የሳዶቅን ልጅ የአሒማዓጽን ሩጫ ይመስለኛል” አለ። ንጉሡም፥ “እርሱ ጥሩ ሰው ነው፤ ቢመጣም የምሥራች ይዞ ነው” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘበኛውም “የመጀመሪያው ሰው የሚሮጠው ልክ እንደ ሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽ ነው” አለ። ንጉሡም “እርሱ ጥሩ ሰው ነው፤ መልካም ወሬ ይዞ ይመጣል” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘበኛውም፥ “የፊተኛው ሩጫ እንደ ሳዶቅ ልጅ እንደ አኪማሖስ ሩጫ ይመስላል” አለ፤ “ንጉሡም፦ እርሱ መልካም ሰው ነው፤ መልካምም ወሬ ያመጣል” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘበኛውም፦ የፊተኛው ሩጫ እንደ ሳዶቅ ልጅ እንደ አኪማአስ ሩጫ ይመስላል አለ፥ ንጉሡም እርሱ መልካም ሰው ነው፥ መልካም ወሬ ያመጣል አለ። |
ከዚያም ጠባቂው ሌላ ሰው ሲሮጥ አይቶ፣ ዘበኛውን ተጣራና፣ “እነሆ ሌላም ሰው ብቻውን እየሮጠ በመምጣት ላይ ነው!” አለ። ንጉሡም፣ “ይኸኛውም መልካም ወሬ ይዞ የመጣ መሆን አለበት” አለ።
ኢዮአብ ገና ተናግሮ ሳይጨርስ፣ የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን ደረሰ፤ አዶንያስም፣ “እንደ አንተ ያለ ታማኝ ሰው መልካም ዜና ሳይዝ አይመጣምና ግባ” አለው።
ጠባቂው፣ “መልእክተኛው ከእነርሱ ዘንድ ደርሷል፤ ነገር ግን ይህም ተመልሶ አልመጣም፤ የወታደሮቹ መሪ ሠረገላ አነዳዱ ልክ እንደ ናሜሲ ልጅ እንደ ኢዩ አነዳድ ነው፤ ሲነዳም እንደ እብድ ነው” ሲል አሳወቀ።
በተራሮች ላይ የቆሙ፣ የምሥራችን የሚያመጡ እግሮች፣ ሰላምን የሚናገሩ፣ መልካም ዜና የሚያበሥሩ፣ ድነትን የሚያውጁ፣ ጽዮንንም፣ “አምላክሽ ነግሧል!” የሚሉ እንዴት ያማሩ ናቸው።