La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 14:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ንጉሡ ሴቲቱን፣ “እኔም ለምጠይቅሽ ነገር አንቺም መልሱን አትደብቂኝ” አላት። ሴቲቱም፣ “ንጉሥ ጌታዬ፤ ዕሺ ይናገር” አለችው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም ንጉሡ ሴቲቱን፥ “የምጠይቅሽን ነገር አንድም ሳትደብቂኝ መልሽልኝ” አላት። ሴቲቱም፥ “ንጉሥ ሆይ! ጠይቀኝ” አለችው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ንጉሡም “አንድ ጥያቄ እጠይቅሻለሁ፤ አንቺም እውነቱን በሙሉ ንገሪኝ” አላት። እርስዋም “ንጉሥ ሆይ! የፈለግኸውን ጠይቀኝ” አለችው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ንጉ​ሡም ለሴ​ቲቱ መልሶ፥ “የም​ጠ​ይ​ቅ​ሽን ነገር አት​ሰ​ው​ሪኝ” አላት። ሴቲ​ቱም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ይና​ገር” አለች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ንጉሡም ለሴቲቱ መልሶ፦ የምጠይቅሽን ነገር አትሰውሪኝ አላት። ሴቲቱም፦ ጌታዬ ንጉሥ ይናገር አለች።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 14:18
5 Referencias Cruzadas  

“አሁንም አገልጋይህ፤ ‘ንጉሥ ጌታዬ በጎውንና ክፉውን በመለየት እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለ ሆነ፣ የጌታዬ የንጉሡ ቃል ያጽናናኝ፤ እግዚአብሔር አምላክህም ካንተው ጋራ ይሁን’ ትላለች።”


ንጉሡም፣ “በዚህ ሁሉ የኢዮአብ እጅ የለበትምን?” ሲል ጠየቃት። ሴቲቱም መልሳ እንዲህ አለች፤ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ ንጉሥ ጌታዬ ከተናገረው ሁሉ ወደ ቀኝም ወደ ግራም የሚል ማንም የለም። አዎን ይህን እንዳደርግ ያዘዘኝና ይህም ሁሉ ቃል በእኔ በአገልጋይህ አንደበት እንዲነገር የላከኝ አገልጋይህ ኢዮአብ ነው።


ንጉሡ ሴዴቅያስ ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ ልኮ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሦስተኛው በር አስመጣውና፤ “አንድ ነገር እጠይቅሃለሁ፤ ምንም አትሸሽገኝ” አለው።


መኳንንቱ ከአንተ ጋራ እንደ ተነጋገርሁ ሰምተው ወደ አንተ ቢመጡና፣ ‘ንጉሡን ምን እንዳልኸው፣ ንጉሡም ምን እንዳለህ ንገረን፤ ሳትደብቅ ንገረን፤ አለዚያ እንገድልሃለን’ ቢሉህ፣