ዳዊትም፣ መልእክተኛውን፣ “እንግዲህ እንዲህ ብለህ ይህን ለኢዮአብ ንገረው፤ ‘መቼም ሰይፍ አንድ ጊዜ ይህን፣ ሌላ ጊዜም ሌላውን ትበላለችና በዚህ አትዘን፤ በከተማዪቱ ላይ ጦርህን አጠንክር’ ” አለው።
2 ሳሙኤል 14:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመሬት ላይ የፈሰሰ ውሃ እንደማይታፈስ ሁሉ፣ እኛም እንደዚሁ እንሞታለን፤ እግዚአብሔር ግን ከአገር የተሰደደ ሰው ከርሱ እንደ ራቀ በዚያው እንዳይቀር የሚመለስበትን ሁኔታ ያመቻቻል እንጂ ሕይወቱ እንድትጠፋ አይፈቅድም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ ሁላችን መሞታችን አይቀሬ ነው፤ በመሬት ላይ እንደ ፈሰሰና ተመልሶም ሊታፈስ እንደማይችል ውሃ ነን፤ እግዚአብሔር የተሰደደ ሰው በስደት በዚያው እንዳይቀር የሚመለስበትን ሁኔታ ያመቻቻል እንጂ ሕይወቱ እንድትጠፋ አይፈቅድም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ ሁላችን መሞታችን የማይቀር ነው፤ እኛ በመሬት ላይ እንደ ፈሰሰና ተመልሶም ሊታፈስ እንደማይችል ውሃ ነን፤ እግዚአብሔር ግን በስደት ላይ የሚገኝ ሰው ከእርሱ እንደ ራቀ እንዳይቀር የሚመለስበትን መንገድ ያዘጋጅለታል እንጂ ሕይወቱ በከንቱ እንድትጠፋ አይፈቅድም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሞትን እንሞታለንና፥ በምድርም ላይ እንደ ፈሰሰና እንደማይመለስ ውኃ እንሆናለንና፥ እግዚአብሔርም ነፍስን ይወስዳል። የተጣለውንም ከእርሱ ያርቅ ዘንድ ያስባል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁላችን እንሞታለን፥ በምድርም ላይ እንደ ፈሰሰና እንደማይመለስ ውኃ ነን፥ እግዚአብሔርም የነፍስን ጥፋት አይወድድም፥ ነገር ግን የተጣለ ሰው ፈጽሞ እንዳይጠፋ በምክሩ ያስባል። |
ዳዊትም፣ መልእክተኛውን፣ “እንግዲህ እንዲህ ብለህ ይህን ለኢዮአብ ንገረው፤ ‘መቼም ሰይፍ አንድ ጊዜ ይህን፣ ሌላ ጊዜም ሌላውን ትበላለችና በዚህ አትዘን፤ በከተማዪቱ ላይ ጦርህን አጠንክር’ ” አለው።
“አሁንም ወደዚህ የመጣሁት ሕዝቡ ስላስፈራኝ ይህንኑ ለንጉሥ ጌታዬ ለመንገር ነው። እኔም አገልጋይህ ይህን አሰብሁ፤ ‘ለንጉሡ እነግረዋለሁ፤ ምናልባትም አገልጋዩ የጠየቀችውን ይፈጽምላት ይሆናል፤
የዕድሜያችን ዘመን ሰባ ዓመት፣ ቢበዛም ሰማንያ ነው፤ ከዚያ በላይ ከሆነም ድካምና መከራ ብቻ ነው፤ ቶሎ ያልፋልና፤ እኛም ወዲያው እንነጕዳለን።
እነዚህም ስድስት ከተሞች ሳያስበው ሰው የገደለ ማንኛውም ሰው እንዲሸሽባቸው ለእስራኤላውያን፣ ለመጻተኞችና በመካከላቸው ለሚኖር ለማንኛውም ሕዝብ የመማፀኛ ቦታዎች ይሆናሉ።
ማኅበሩም በነፍሰ ገዳይነት የተከሰሰውን ሰው ከደመኛው እጅ በማስጣል ወደ ሸሸበት ወደ መማጸኛው ከተማ ይመልሰው፤ የተቀደሰ ዘይት የተቀባው ሊቀ ካህን እስኪሞትም ድረስ በዚያ ይቈይ።
ደቀ መዛሙርታቸውን ከሄሮድስ ወገኖች ጋራ ወደ እርሱ ልከው እንዲህ አሉት፤ “መምህር ሆይ፤ አንተ እውነተኛና የእግዚአብሔርንም መንገድ በእውነት የምታስተምር እንደ ሆንህ፣ ለማንም ሳታደላ ሁሉን እኩል እንደምትመለከት እናውቃለን፤
አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፣ የጌቶች ጌታ ታላቅ አምላክ፣ ኀያልና የሚያስፈራ፣ አድልዎ የማያደርግ፣ መማለጃም የማይቀበል ነውና።
ለሰው ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደየሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ፣ በዚህ ምድር በእንግድነት ስትኖሩ በፍርሀት ኑሩ።