2 ሳሙኤል 13:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትዕማርም በራሷ ላይ ዐመድ ነሰነሰች፤ ጌጠኛ ልብሷን ቀደደች፤ ከዚያም እጇን በራሷ ላይ አድርጋ እያለቀሰች ሄደች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትዕማርም በራሷ ላይ ዐመድ ነስንሳ፤ ለብሳው የነበረውን መጐናጸፊያ ቀዳደደች፤ እጇንም በራሷ ላይ አድርጋ እያለቀሰች ሄደች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትዕማርም አመድ ወስዳ በራስዋ ላይ ነሰነሰች፤ በላይዋ የነበረውንም ብዙ ኅብር ያለውን ልብስዋን ቀደደችው፤ እጅዋንም በራስዋ ላይ ጭና እየጮኸች ሄደች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትዕማርም በራስዋ ላይ አመድ ነስንሳ፥ ብዙ ኅብርም ያለውን ልብስዋን ተርትራ፥ እጅዋንም በራስዋ ላይ ጭና እየጮኸች ሄደች። |
በሦስተኛውም ቀን የተቀደደ ልብስ የለበሰ፣ በራሱም ላይ ትቢያ የነሰነሰ አንድ ሰው ከሳኦል ሰፈር መጣ። ወደ ዳዊት እንደ ደረሰም፣ ወደ መሬት ለጥ ብሎ በአክብሮት እጅ ነሣ።
ወንድሟ አቤሴሎምም፣ “ያ ወንድምሽ አምኖን ካንቺ ጋራ ነበርን? እኅቴ ሆይ፣ አሁን ዝም በዪ፤ ወንድምሽ ስለ ሆነ፤ ነገሩን በልብሽ አትያዢው” አላት። ትዕማርም በወንድሟ በአቤሴሎም ቤት ብቸኛ ሴት ሆና ኖረች።
መርዶክዮስ የተደረገውን ሁሉ ባወቀ ጊዜ፣ ልብሱን ቀደደ፤ ከዚያም ማቅ ለብሶ፣ በራሱ ላይ ዐመድ ነስንሶ ድምፁን ከፍ በማድረግ አምርሮ እየጮኸ ወደ ከተማዪቱ መካከል ወጣ።
እነርሱም ከሩቅ ሆነው ሲመለከቱት እርሱ መሆኑን ሊለዩ አልቻሉም፤ በዚህ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ ልብሳቸውንም ቀድደው በራሳቸው ላይ ትቢያ ነሰነሱ።
በዚህ ጊዜ ኢያሱ ልብሱን ቀደደ፤ በእግዚአብሔርም ታቦት ፊት በግንባሩ ተደፋ፤ የእስራኤል ሽማግሌዎችም እንደዚሁ አደረጉ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።