2 ሳሙኤል 11:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአብም በጦርነቱ የሆነውን ሁሉ ለዳዊት ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ኢዮአብ በጦርነቱ የሆነውን ሁሉ ለዳዊት ላከ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢዮአብ ስለ ጦርነቱ የሚያስረዳ መልእክት ወደ ዳዊት ላከ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም የጦርነቱን ዜና ሁሉ ለዳዊት ይነግሩት ዘንድ ላከ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም ልኮ በሰልፍ የሆነውን ሁሉ ለዳዊት ነገረው። |
መልእክተኛው እንደ ደረሰም፣ ለኢዩ፣ “የንጉሡን ልጆች ራስ አምጥተዋል” ብሎ ነገረው። ከዚያም ኢዩ፣ “በከተማዪቱ መግቢያ በር ላይ ሁለት ቦታ ከምራችሁ እስከ ነገ ጧት ድረስ አቈዩአቸው” ብሎ አዘዘ።