ዳዊትም፣ “ምን ነገር ተፈጠረ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “ሰዎቹ ከጦርነቱ ሸሽተዋል፤ ብዙዎቹ ወድቀዋል፤ ሞተዋል፤ ሳኦልና ልጁ ዮናታንም ሞተዋል” አለ።
2 ሳሙኤል 1:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዳዊት ወሬውን የነገረውን ወጣት፣ “ሳኦልና ልጁ ዮናታን መሞታቸውን እንዴት ዐወቅህ?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ዳዊት ወሬውን የነገረውን ወጣት፥ “ሳኦልና ልጁ ዮናታን መሞታቸውን እንዴት አወቅህ?” ሲል ጠየቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ወሬ ያመጣውን ወጣት “ሳኦልና ልጁ ዮናታን መሞታቸውን እንዴት ዐወቅህ?” ሲል ጠየቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ወሬውን ያመጣለትን ጐልማሳ፥ “ሳኦልና ልጁ ዮናታን እንደ ሞቱ እንዴት ዐወቅህ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ወሬኛውን ጕልማሳ፦ ሳኦልና ልጁ ዮናታን እንደ ሞቱ በምን ታውቃለህ? አለው። |
ዳዊትም፣ “ምን ነገር ተፈጠረ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “ሰዎቹ ከጦርነቱ ሸሽተዋል፤ ብዙዎቹ ወድቀዋል፤ ሞተዋል፤ ሳኦልና ልጁ ዮናታንም ሞተዋል” አለ።
ወሬ ነጋሪው ወጣትም እንዲህ አለ፤ “ድንገት ወደ ጊልቦዓ ተራራ ወጥቼ ነበር፤ እዚያም ሳኦል ጦሩን ተደግፎ ሳለ፣ የሠረገሎችና የፈረሰኞች አለቆች ተከታተሉት።