Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 14:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 አላዋቂው ሰው ሁሉን ያምናል፤ አስተዋይ ግን ርምጃውን ያስተውላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል፥ ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሞኝ ሰው የሚነግሩትን ሁሉ አምኖ ይቀበላል፤ ብልኆች ግን እርምጃቸውን በጥንቃቄ ይመረምራሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የዋህ ነገርን ሁሉ ያምናል፤ ዐዋቂ ግን ወደ ንስሓ ይመለሳል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 14:15
16 Referencias Cruzadas  

ከዚያም ዳዊት ወሬውን የነገረውን ወጣት፣ “ሳኦልና ልጁ ዮናታን መሞታቸውን እንዴት ዐወቅህ?” ሲል ጠየቀው።


ቤርሳቤህም፣ “መልካም ነው፤ ይህንኑ ለንጉሡ እነግርልሃለሁ” ብላ መለሰች።


አራት ጊዜም ይህንኑ ዐይነት መልእክት ላኩብኝ፤ እኔም በእያንዳንዱ ጊዜ ያንኑ መልስ ሰጠሁ።


ልባቸውን ከጽድቅ የሚመልሱ የእጃቸውን ሙሉ ዋጋ ይቀበላሉ፤ ደግ ሰውም ወሮታውን ያገኛል።


ጠቢብ ሰው ጥንቁቅ ነው፤ ከክፉም ይርቃል፤ ሞኝ ግን ችኵልና ደንታ ቢስ ነው።


የአስተዋዮች ጥበብ መንገዳቸውን ልብ ማለት ነው፤ የሞኞች ቂልነት ግን መታለል ነው።


እኩይ ሰው ክፉ ንግግር ያዳምጣል፤ ሐሰተኛም የተንኰለኛን አንደበት በጥንቃቄ ይሰማል።


አስተዋይ ክፉን አይቶ ራሱን ይሸሽጋል፤ አላዋቂዎች ግን በዚያው ይቀጥላሉ፤ ይቀጡበታልም።


አስተዋይ ክፉን አይቶ ራሱን ይሸሽጋል፤ አላዋቂዎች ግን በዚያው ይቀጥላሉ፤ ይቀጡበታልም።


የእግርህን ጐዳና አስተካክል፤ የጸናውን መንገድ ብቻ ያዝ።


ስለዚህ አስተዋይ ሰው በእንዲህ ያለ ጊዜ ዝም ይላል፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና።


እርሱም ሰርግዮስ ጳውሎስ ከተባለው አስተዋይ አገረ ገዥ ጋራ ነበረ። ይህ አገረ ገዥ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ፈልጎ በርናባስንና ሳውልን አስጠራቸው።


ከእንግዲህ በማዕበል ወደ ፊትና ወደ ኋላ እየተነዳን፣ በልዩ ልዩ ዐይነት የትምህርት ነፋስ፣ በሰዎችም ረቂቅ ተንኰልና ማታለል ወዲያና ወዲህ እየተንገዋለልን ሕፃናት አንሆንም።


ስለዚህ ሞኞች አትሁኑ፤ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ።


ወዳጆች ሆይ፤ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር መሆናቸውን መርምሩ፤ ምክንያቱም ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos