2 ሳሙኤል 1:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ኀያላኑ እንዴት ወደቁ! የጦር መሣሪያዎቹስ እንዴት ከንቱ ይሁኑ!” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኀያላን እንዴት ወደቁ! የጦር መሣሪያዎቹስ እንዴት ጠፉ!” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ኀያላን እንዴት ወደቁ? የጦር መሣሪያዎቹስ እንዴት ጠፉ?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀያላን እንዴት ወደቁ! የሰልፍም ዕቃዎች እንዴት ጠፉ!” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃያላን እንዴት ወደቁ! የሰልፍም ዕቃ እንዴት ጠፋ! |
በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ ለሞት ባደረሰው ሕመም ታምሞ ነበር። የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ሊጠይቀው ወርዶ አለቀሰለት፤ “ወየው አባቴን! ወየው አባቴን! ወየው የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች!” እያለም ጮኸ።
ኤልሳዕም ይህን አይቶ፣ “አባቴ አባቴ የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች!” ብሎ ጮኸ፤ ዳግመኛም ኤልያስን አላየውም፤ ከዚያም የገዛ ልብሱን ይዞ ከሁለት ቦታ ቀደደው።