እርሷም መልሳ፣ “አምላክህን ሕያው እግዚአብሔርን! በማድጋ ካለው ዕፍኝ ዱቄትና በማሰሮ ካለው ጥቂት ዘይት በቀር ምንም የለኝም። እነሆ፤ ለራሴና ለልጄ ምግብ አዘጋጅቼ በልተን እንድንሞት ጭራሮ ለቃቅሜ ወደ ቤት ልወስድ ነው” አለችው።
2 ነገሥት 4:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤልሳዕም፣ “ታዲያ እኔ ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ? በቤትሽ ምን እንዳለ ንገሪኝ” አላት። እርሷም፣ “አገልጋይህ ከጥቂት ዘይት በቀር በቤቷ ምንም ነገር የላትም” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልሳዕም “ታዲያ ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ? በቤትሽም ምን እንዳለሽ ንገሪኝ” ሲል ጠየቃት። እርሷም “በትንሽ ማሰሮ ከሚገኝ የወይራ ዘይት በቀር ሌላ ምንም የለኝም” ስትል መለሰች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልሳዕም “ታዲያ ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ? በቤትሽም ምን እንዳለሽ ንገሪኝ” ሲል ጠየቃት። እርስዋም “በትንሽ ማሰሮ ከሚገኝ የወይራ ዘይት በቀር ሌላ ምንም የለኝም” ስትል መለሰች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልሳዕም፥ “አደርግልሽ ዘንድ ምን ትሻለሽ? በቤትሽም ያለውን ንገሪኝ” አላት። እርስዋም፥ “ለእኔ ለአገልጋይህ ከዘይት ማሰሮ በቀር በቤቴ አንዳች የለኝም” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤልሳዕም “አደርግልሽ ዘንድ ምን ትሻለሽ? በቤትሽ ያለውን ንገሪኝ፤” አላት። እርስዋም “ለእኔ ለባሪያህ ከዘይት ማሰሮ በቀር በቤቴ አንዳች የለኝም፤” አለች። |
እርሷም መልሳ፣ “አምላክህን ሕያው እግዚአብሔርን! በማድጋ ካለው ዕፍኝ ዱቄትና በማሰሮ ካለው ጥቂት ዘይት በቀር ምንም የለኝም። እነሆ፤ ለራሴና ለልጄ ምግብ አዘጋጅቼ በልተን እንድንሞት ጭራሮ ለቃቅሜ ወደ ቤት ልወስድ ነው” አለችው።
ከተሻገሩ በኋላም ኤልያስ ኤልሳዕን፤ “ከአንተ ከመወሰዴ በፊት ምን ላደርግልህ እንደምትፈልግ ንገረኝ” አለው። ኤልሳዕም፣ “መንፈስህ በዕጥፍ እንዲያድርብኝ እለምንሃለሁ” ብሎ መለሰ።
ጴጥሮስ ግን፣ “እኔ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ነገር ግን ያለኝን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥተህ በእግርህ ተመላለስ” አለው፤
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለጠጋ እንዲሆኑና እርሱን ለሚወድዱም ተስፋ የተሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?