2 ነገሥት 23:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮስያስም፣ “በሉ እንዳለ ተዉት፤ ዐፅሙን ማንም ሰው ከቦታው እንዳያንቀሳቅሰው” አለ፤ ስለዚህ የእርሱንና ከሰማርያ የመጣውን ነቢይ ዐፅም ሳይነኩ እንዳለ ተውት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮስያስም “እንዳለ ይኑር፤ ተውት፤ የእርሱ ዐፅም ከዚህ መንቀሳቀስ የለበትም!” ሲል መለሰ። ስለዚህም የእርሱም ሆነ የሰማርያው ነቢይ ዐፅሞች ከዚያ እንዲነሡ አልተደረገም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮስያስም “እንዳለ ይኑር፤ ተዉት፤ የእርሱ ዐፅም ከዚህ መንቀሳቀስ የለበትም!” ሲል መለሰ። ስለዚህም የእርሱም ሆነ የሰማርያው ነቢይ ዐፅሞች ከዚያ እንዲነሡ አልተደረገም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “ተዉት፥ ማንም አጥንቱን አያንቀሳቅሰው” አለ፤ አጥንቶቹም ከሰማርያ ከመጣው ከነቢዩ አጥንት ጋር ዳኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም “ተዉት፤ ማንም አጥንቱን አያንቀሳቅሰው፤” አለ፤ እነርሱም ከሰማርያ ከወጣው ከነቢዩ አጥንት ጋር አጥንቱን ተዉ። |
ከቀበሩትም በኋላ ልጆቹን እንዲህ አላቸው፤ “እኔም በምሞትበት ጊዜ የእግዚአብሔር ሰው በተቀበረበት መቃብር ቅበሩኝ፤ ዐጥንቶቼንም በዐጥንቶቹ አጠገብ አኑሩ።