አሞን በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሁለት ዓመት ገዛ፤ እናቱ ሜሶላም ትባላለች፤ እርሷም የዮጥባ አገር ሰው የሐሩስ ልጅ ነበረች።
2 ነገሥት 21:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምናሴም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ “የዖዛ አትክልት” በሚባለው በቤተ መንግሥቱ አትክልት ውስጥ ተቀበረ። ልጁ አሞንም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምናሴ ሞተ፤ በቤተ መንግሥቱ ግቢ “የዑዛ የአትክልት ስፍራ” ተብሎ በሚጠራው ቦታ ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አሞን ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምናሴ ሞተ፤ በቤተ መንግሥቱ ግቢ “የዑዛ የአትክልት ስፍራ” ተብሎ በሚጠራው ቦታ ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አሞን ነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምናሴም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በቤቱም አጠገብ ባለው በዖዛ አትክልት ቦታ ተቀበረ፤ ልጁም አሞጽ በእርሱ ፋንታ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምናሴም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በቤቱም አጠገብ ባለው በዖዛ አትክልት ተቀበረ፤ ልጁም አሞን በእርሱ ፋንታ ነገሠ። |
አሞን በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሁለት ዓመት ገዛ፤ እናቱ ሜሶላም ትባላለች፤ እርሷም የዮጥባ አገር ሰው የሐሩስ ልጅ ነበረች።
ኢዮራም ሲነግሥ ዕድሜው ሠላሳ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ስምንት ዓመት ገዛ። በሞተ ጊዜም ማንም አላዘነለትም፤ በዳዊት ከተማ እንጂ በነገሥታቱ መቃብር አልቀበሩትም።
ሶርያውያንም በወጡ ጊዜ ኢዮአስን ክፉኛ አቍስለው፣ ጥለውት ሄዱ፤ የካህኑን የዮዳሄን ልጅ ስለ ገደለም፣ ሹማምቱ አሢረውበት በዐልጋው ላይ እንዳለ ገደሉት። በዚህ ሁኔታም ሞቶ በዳዊት ከተማ ተቀበረ እንጂ በነገሥታቱ መቃብር አልተቀበረም።
አካዝ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በኢየሩሳሌምም ከተማ ተቀበረ፤ የተቀበረው ግን በእስራኤል ነገሥታት መካነ መቃብር አልነበረም። ልጁ ሕዝቅያስም በምትኩ ነገሠ።
ሕዝቅያስም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ የዳዊት ዘሮች መካነ መቃብር በሆነው ኰረብታም ተቀበረ። በሞተም ጊዜ ይሁዳ ሁሉና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በሙሉ አከበሩት። ልጁ ምናሴም በእግሩ ተተካ።
በይሁዳ ንጉሥ በአሞን ልጅ በኢዮስያስ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ፣ ወደ አማርያ ልጅ፣ ወደ ጎዶልያስ ልጅ፣ ወደ ኵሲ ልጅ ወደ ሶፎንያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤