የከተማዪቱም ሰዎች ኤልሳዕን፣ “እነሆ ጌታችን፤ እንደምታያት ይህች ከተማ ለኑሮ የተመቸች ናት፤ ይሁን እንጂ ውሃው መጥፎ ሲሆን ምድሪቱም ፍሬ የማትሰጥ ናት” አሉት።
2 ነገሥት 2:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “እስኪ በአዲስ ማሰሮ ጨው ጨምራችሁ አምጡልኝ” አለ፤ እንዳለውም አመጡለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልሳዕም “በአዲስ አፍላል ማሰሮ ውስጥ ጨው ጨምራችሁ አምጡልኝ” ብሎ አዘዘ። እነርሱም እንዳዘዛቸው አድርገው አመጡለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልሳዕም “በአዲስ አፍላል ማሰሮ ውስጥ ጨው ጨምራችሁ አምጡልኝ” ብሎ አዘዘ። እነርሱም እንዳዘዛቸው አድርገው አመጡለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “አዲስ ማሰሮ አምጡልኝ፤ ጨውም ጨምሩበት” አለ፤ ያንም አመጡለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም “አዲስ ማሰሮ አምጡልኝ፤ ጨውም ጨምሩበት፤” አለ፤ ያንንም አመጡለት። |
የከተማዪቱም ሰዎች ኤልሳዕን፣ “እነሆ ጌታችን፤ እንደምታያት ይህች ከተማ ለኑሮ የተመቸች ናት፤ ይሁን እንጂ ውሃው መጥፎ ሲሆን ምድሪቱም ፍሬ የማትሰጥ ናት” አሉት።
ከዚያም ወደ ውሃው ምንጭ ሄዶ ጨው ጣለበትና “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ይህን ውሃ ፈውሼዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ለሞት ምክንያት አይሆንም፤ ምድሪቱንም ፍሬ እንዳትሰጥ አያደርጋትም’ አለ።”
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ሞዓብ እንደ ሰዶም፣ አሞናውያን እንደ ገሞራ፣ ዐረም እንደ ዋጠው ቦታና እንደ ጨው ጕድጓድ ለዘላለም ጠፍ ይሆናሉ። ከሕዝቤ የቀሩት ይዘርፏቸዋል፤ ከወገኔ የተረፉትም ምድራቸውን ይወርሳሉ።”