በዚያ መኖር እንደ ጀመሩም እግዚአብሔርን አይፈሩትም ነበር፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አንበሶች ሰደደባቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹን ሰብረው ገደሉ።
2 ነገሥት 17:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአሦርም ንጉሥ፣ “ወደ ሰማርያ ከተሞች ወስደህ ያሰፈርኸው ሕዝብ የዚያ አገር አምላክ የሚፈልገውን አላወቀም፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ሰብሮ የሚገድል አንበሳ ላከበት” የሚል ወሬ ደረሰው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአሦርም ንጉሠ ነገሥት “በሰማርያ ከተሞች ሰፍረው እንዲኖሩ ያደረግሃቸው ሕዝቦች የዚያችን አገር አምላክ ሕግ የሚያውቁ ሆነው አልተገኙም፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ሰባብሮ የሚገድሉ አንበሶችን ላከባቸው” የሚል ወሬ ደረሰው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአሦርም ንጉሠ ነገሥት “በሰማርያ ከተሞች ሰፍረው እንዲኖሩ ያደረግሃቸው ሕዝቦች የዚያችን አገር አምላክ ሕግ የሚያውቁ ሆነው አልተገኙም፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ሰባብሮ የሚገድሉ አንበሶችን ላከባቸው” የሚል ወሬ ደረሰው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም ለአሦር ንጉሥ፥ “ያፈለስኻቸው፥ በሰማርያም ከተሞች ያኖርኻቸው ሕዝቦች የሀገሩን አምላክ ሕግ አላወቁም፤ የሀገሩን አምላክ ሕግ አላወቁምና አንበሶችን ሰድዶባቸዋል፤ እነሆም፥ እየገደሉአቸው ነው” ብለው ተናገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም ለአሦር ንጉሥ “ያፈለስኻቸው፥ በሰማርያም ከተሞች ያኖርኻቸው የአገሩን አምላክ ወግ አላወቁም፤ የአገሩን አምላክ ወግ አላወቁምና አንበሶችን ሰድዶባቸዋል፤ እነሆም፥ ገደሉአቸው፤” ብለው ተናገሩት። |
በዚያ መኖር እንደ ጀመሩም እግዚአብሔርን አይፈሩትም ነበር፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አንበሶች ሰደደባቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹን ሰብረው ገደሉ።
ከዚያም የአሦር ንጉሥ፣ “ከሰማርያ ማርካችሁ ካመጣችኋቸው ካህናት አንዱን፣ በዚያው እንዲኖር መልሳችሁ ውሰዱትና የአገሩ አምላክ ምን እንደሚፈልግ ሕዝቡን ያስተምር” ሲል አዘዘ።
በሰማርያ በደል የሚምሉ፣ ወይም፣ ‘ዳን ሆይ፤ ሕያው አምላክህን’ የሚሉ፣ ወይም ‘ሕያው የቤርሳቤህ አምላክን’ ብለው የሚምሉ፣ ዳግመኛ ላይነሡ፣ ለዘላለም ይወድቃሉ።”
ሳሙኤልም ለንጉሥ የሚገባውን ወግና ሥርዐት ለሕዝቡ ገልጾ ካስረዳ በኋላ በመጽሐፍ ጽፎ በእግዚአብሔር ፊት አኖረው። ከዚህ በኋላ ሳሙኤል እያንዳንዱን ሰው ወደየቤቱ አሰናበተ።