እስራኤልም ሁሉ አልቅሰው ይቀብሩታል። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከኢዮርብዓም ቤት ሁሉ መልካም ነገር ያገኘበት እርሱ ብቻ ስለ ሆነ፣ በወግ በማዕርግ የሚቀበር እርሱ ብቻ ነው።
2 ነገሥት 13:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአካዝ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በሰማርያም ተቀበረ። ልጁ ዮአስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአካዝ ሞተ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ዮአስ ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአካዝ ሞተ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ዮአስ ነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በሰማርያም ቀበሩት፥ ልጁም ዮአስ በፋንታው ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ቀበሩት፤ ልጁም ዮአስ በፋንታው ነገሠ። |
እስራኤልም ሁሉ አልቅሰው ይቀብሩታል። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከኢዮርብዓም ቤት ሁሉ መልካም ነገር ያገኘበት እርሱ ብቻ ስለ ሆነ፣ በወግ በማዕርግ የሚቀበር እርሱ ብቻ ነው።
በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአስ ዘመን፣ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፣ የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ በሰማርያ ከተማ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ዐሥራ ስድስት ዓመትም ገዛ።
ከዚያም አሜስያስ የኢዩ የልጅ ልጅ፣ የኢዮአካዝ ልጅ ወደ ሆነው ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ዮአስ፣ “ናና ፊት ለፊት እንጋጠም” ሲል መልእክተኞች ላከበት።