2 ነገሥት 13:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ግን ራራላቸው፤ ዐዘነላቸው፤ ፊቱን መለሰላቸው፤ ይህም ከአብርሃም፣ ከይሥሐቅና ከያዕቆብ ጋራ ስለ ገባው ኪዳን ሲል ነው፤ እስከ ዛሬ ድረስ ሊያጠፋቸው አልፈለገም፤ ከፊቱም አላስወገዳቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ግን በቸርነቱ ምሕረትን በማድረግ ረዳቸው እንጂ እንዲደመሰሱ አልፈቀደም፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የሰጠውን ቃል ኪዳን በማሰብ ሕዝቡን ስላልረሳው ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ግን በቸርነቱ ምሕረትን በማድረግ ረዳቸው እንጂ እንዲደመሰሱ አልፈቀደም፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የሰጠውን ቃል ኪዳን በማሰብ ሕዝቡን ስላልረሳው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ግን ራራላቸው፤ ማራቸውም፤ ከአብርሃምና ከይስሐቅ፥ ከያዕቆብም ጋር ስላደረገው ቃል ኪዳን እነርሱን ተመለከተ፤ ሊያጠፋቸውም አልወደደም፤ ፈጽሞም ከፊቱ አልጣላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ግን ራራላቸው፤ ማራቸውም፤ ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር ስላደረገውም ቃል ኪዳን እነርሱን ተመለከተ፤ ሊያጠፋቸውም አልወደደም፤ ፈጽሞም ከፊቱ አልጣላቸውም። |
ይሁን እንጂ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ የባሪያህን ጸሎትና ስለ ምሕረት ያቀረበውን ልመና አድምጥ፤ በዛሬው ዕለት ባሪያህ በፊትህ የሚያቀርበውን ጩኸትና ጸሎት ስማ።
እግዚአብሔር በባሪያዎቹ በነቢያት ሁሉ አማካይነት ባስጠነቀቃቸው መሠረት፣ ከፊቱ እስኪያስወግዳቸው ድረስ በዚያው ቀጠሉበት፤ ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ከሀገሩ ተማርኮ ወደ አሦር ተወሰደ፤ አሁንም በዚያው ይገኛል።
እንግዲህ ይህ ሁሉ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሊደርስ የቻለው ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ነበር፤ በመጨረሻም ከፊቱ አስወገዳቸው። በዚህ ጊዜ ሴዴቅያስ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “መልካምነቴ ሁሉ በፊትህ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤ በፊትህም ስሜን እግዚአብሔርን ዐውጃለሁ፤ የምምረውን እምረዋለሁ፤ የምራራለትንም ራራለታለሁ፤
በዚያ ጊዜ ከያዕቆብ ጋራ የገባሁትን ኪዳኔን፣ ከይሥሐቅም ጋራ የገባሁትን ኪዳኔን፣ ደግሞም ከአብርሃም ጋራ የገባሁትን ኪዳኔን ዐስባለሁ፤ ምድሪቱንም ዐስባታለሁ።
“ከዚያም በግራው በኩል ላሉት ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ፤ ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው የዘላለም እሳት ከእኔ ተለይታችሁ ሂዱ፤
ከዚያም በመካከላቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወገዱ፤ እግዚአብሔርንም አመለኩ፤ እግዚአብሔርም እስራኤል ስትጐሳቈል ዝም ብሎ ማየት አልቻለም።