እርሷም ኤልያስን፤ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ እኔ ምን አደረግሁህ? እዚህ የመጣኸው ኀጢአቴን አስታውሰህ ልጄን ለመግደል ነውን?” አለችው።
2 ነገሥት 1:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ንጉሡ አንድ የዐምሳ አለቃ ከዐምሳ ወታደሮቹ ጋራ ወደ ኤልያስ ላከ። የዐምሳ አለቃውም ኤልያስ ወደ ተቀመጠበት ኰረብታ ጫፍ ወጥቶ፣ “አንተ የእግዚአብሔር ሰው፤ ንጉሡ፣ ‘ና ውረድ’ ይልሃል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ንጉሡ አንዱን የጦር መኰንን ከኀምሳ ሰዎች ጋር ሄዶ ኤልያስን ይዞ ያመጣለት ዘንድ አዘዘው፤ መኰንኑም ኤልያስን በአንድ ኰረብታ ላይ ተቀምጦ አገኘውና “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ወርደህ ወደ እርሱ እንድትመጣ ንጉሡ አዞሃል” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ንጉሡ አንዱን የጦር መኰንን ከኀምሳ ሰዎች ጋር ሄዶ ኤልያስን ይዞ ያመጣለት ዘንድ አዘዘው፤ መኰንኑም ኤልያስን በአንድ ኰረብታ ላይ ተቀምጦ አገኘውና “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ወርደህ ወደ እርሱ እንድትመጣ ንጉሡ አዞሃል” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ይጠሩት ዘንድ የአምሳ አለቃውን ከአምሳ ሰዎች ጋር ወደ እርሱ ላከ፤ ወደ እርሱም ሄዱ፤ እነሆም፥ በተራራ ራስ ላይ ተቀምጦ አገኙት። የአምሳ አለቃውም፥ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ንጉሡ ይጠራሃል ፈጥነህ ና፤ ውረድ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም የአምሳ አለቃውን ከአምሳ ሰዎች ጋር ሰደደ፤ ወደ እርሱም ወጣ፤ እነሆም፥ በተራራ ራስ ላይ ተቀምጦ ነበር። እርሱም “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ንጉሡ ‘ውረድ’ ይልሃል፤” አለው። |
እርሷም ኤልያስን፤ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ እኔ ምን አደረግሁህ? እዚህ የመጣኸው ኀጢአቴን አስታውሰህ ልጄን ለመግደል ነውን?” አለችው።
አምላክህን ሕያው እግዚአብሔርን! ጌታዬ አንተን ለመፈለግ መልእክተኛ ያልላከበት ሕዝብና መንግሥት የለም፤ የትኛውም ሕዝብ ሆነ መንግሥት አንተ በዚያ አለመኖርህን ባስታወቀው ጊዜ ሁሉ አንተን አለማግኘቱን ለማረጋገጥ ያስምለው ነበር።
ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት እያስገደለች በነበረበት ጊዜ፣ አብድዩ መቶውን ነቢያት ወስዶ ዐምሳ ዐምሳውን በሁለት ዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውሃ ይሰጣቸው ነበር።
ስለዚህም እርሷ፣ “ነገ በዚህ ሰዓት ያንተንም ነፍስ ከእነዚያ እንደ አንዱ ነፍስ ሳላደርጋት ብቀር አማልክት እንዲህ ያድርጉብኝ፤ ከዚህ የባሰም ያምጡብኝ” ስትል ወደ ኤልያስ መልእክተኛ ላከች።
የእስራኤልም ንጉሥ ለኢዮሣፍጥ፣ “መኖሩንማ በርሱ አማካይነት የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምንጠይቀው አንድ ነቢይ አሁንም አለ፤ ነገር ግን ስለ እኔ ክፉ እንጂ ምን ጊዜም መልካም ትንቢት ተናግሮ ስለማያውቅ እጠላዋለሁ፤ ይህም ሰው የይምላ ልጅ ሚክያስ ነው” አለ። ኢዮሣፍጥም፣ “ንጉሡ እንዲህ ማለት አይገባውም” ሲል መለሰ።
ስለዚህ ተነሥታ የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሄደች። የእግዚአብሔር ሰው በሩቁ ሲያያት አገልጋዩን ግያዝን እንዲህ አለው፤ “ሱነማዪቱን አየሃት፤ ያቻትና!
ወደ እግዚአብሔር ቤት አመጣኋቸው፤ ወደ ሐናን ልጆች ክፍልም አስገባኋቸው፤ የሐናን አባት ጌዴልያም የእግዚአብሔር ሰው ነበረ። ክፍሉም በመኳንንቱ ክፍል አጠገብ፣ ከመዕሤያ ክፍል በላይ ነበር፤ መዕሤያም የበር ጠባቂው የሰሎም ልጅ ነበረ፤
እሾኽ ጐንጕነው አክሊል በመሥራት ራሱ ላይ ደፉበት፤ የሸንበቆ በትር በቀኝ እጁ በማስያዝ በፊቱ ተንበርክከው፣ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን” በማለት አሾፉበት፤
በመንገድ የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ የስድብ ናዳ በማውረድ እንዲህ ይሉት ነበር፤ “አዪ፤ አንተ ቤተ መቅደስን አፍርሰህ በሦስት ቀን የምትሠራ፤
አይተን እናምን ዘንድ ይህ ክርስቶስ፣ ይህ የእስራኤል ንጉሥ እስኪ ከመስቀል ይውረድ።” ከርሱ ጋራ የተሰቀሉትም እንደዚሁ የስድብ ናዳ ያወርዱበት ነበር።
ደቀ መዛሙርቱም ያዕቆብና ዮሐንስ ይህን ሲያዩ፣ “ጌታ ሆይ፤ ኤልያስ እንዳደረገው ሁሉ እሳት ከሰማይ ወርዶ እንዲያጠፋቸው እንድናዝዝ ትፈቅዳለህን?” አሉት።
ሳኦልም ይህ በተነገረው ጊዜ ሌሎች ሰዎች ላከ፤ እነርሱም ትንቢት ተናገሩ፤ ሳኦል ለሦስተኛ ጊዜ ሰዎች ላከ፣ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ።