La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 26:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዳዊትም ለአበኔር እንዲህ አለ፤ “አንተ ብርቱ ሰው ነህ? በእስራኤልስ ዘንድ አንተን የሚመስል ማን ነው? እነሆ፤ አንድ ሰው ንጉሡን ጌታህን ለመግደል መጥቶ ነበር፤ ታዲያ አንተ ንጉሥ ጌታህን ያልጠበቅኸው ስለ ምንድን ነው?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዳዊትም እንዲህ አለ፤ “አንተ ብርቱ ሰው አይደለህምን? በእስራኤልስ ዘንድ አንተን የሚመስል ማን ነው? እነሆ፤ አንድ ሰው ንጉሡን ጌታህን ለመግደል መጥቶ ነበር፤ ታዲያ አንተ ንጉሥ ጌታህን ያልጠበቅኸው ስለ ምንድነው?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዳዊትም “አበኔር! አንተ በእስራኤል የታወቅህ ታላቅ ሰው አይደለህምን? ታዲያ ጌታህን ንጉሡን በደንብ የማትጠብቀው ስለምንድን ነው? እነሆ፥ ከእኛ አንድ ሰው ጌታህን ለመግደል ወደ ሰፈር ገብቶ ነበር፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም አቤ​ኔ​ርን፥ “አንተ ጐል​ማሳ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አን​ተን የሚ​መ​ስል ማን ነው? ጌታ​ህን ንጉ​ሡን ለመ​ግ​ደል አንድ ሰው ገብቶ ነበ​ርና ጌታ​ህን ንጉ​ሡን የማ​ት​ጠ​ብቅ ስለ​ምን ነው?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም አበኔርን፦ አንተ ጕልማሳ አይደለህምን? በእስራኤል ዘንድ አንተን የሚመስል ማን ነው? ጌታህን ንጉሡን ለመግደል አንድ ሰው ገብቶ ነበርና ጌታህን ንጉሡን የማትጠብቅ ስለ ምን ነው?

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 26:15
5 Referencias Cruzadas  

ከዚያም ንጉሡ ለራሱ ሰዎች እንዲህ አለ፤ “በዛሬዪቱ ዕለት በእስራኤል መስፍንና ታላቅ ሰው መውደቁን አላወቃችሁምን?


ከዚያም ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል ለጥቂት ጊዜ በጣም ታወከ፤ ሐሳቡም አስደነገጠው። ንጉሡም፣ “ብልጣሶር ሆይ፤ ሕልሙም ሆነ ትርጕሙ አያስደንግጥህ” አለው። ብልጣሶርም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “ሕልሙ ለሚጠሉህ ይሁን፤ ትርጕሙም ለጠላቶችህ!


ከዚያም ተመልሶ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሲመጣ፣ ተኝተው አገኛቸው፤ ጴጥሮስንም እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ፤ ከእኔ ጋራ ለአንድ ሰዓት እንኳ መትጋት አቃታችሁን?


ዳዊት ሰራዊቱንና የኔርን ልጅ አብኔርን፣ “አበኔር ሆይ፣ አትመልስልኝምን?” ሲል ተጣራ። አበኔርም፣ “በንጉሡ ላይ የምትጮኽ አንተ ማነህ?” በማለት መለሰ።


ያደረግኸው መልካም አይደለም፤ ሕያው እግዚአብሔርን! አንተና ሰዎችህ ሞት ይገባችኋል፤ እግዚአብሔር የቀባውን ጌታችሁን አልጠበቃችሁምና። እስኪ ተመልከት፤ በራስጌው የነበሩት የንጉሡ ጦርና የውሃ መያዣ የት አሉ?”