1 ሳሙኤል 24:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም ለሳኦል ማለለት፤ ከዚያም ሳኦል ወደ ቤቱ ተመለሰ። ዳዊትና ሰዎቹ ግን ወደ ዐምባው ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘሮቼን እንዳታጠፋ ስሜንም ከአባቴ ቤት እንዳትደመስስ አሁን በጌታ ማልልኝ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ይህን እንደሚያደርግ ማለለት። ከዚህ በኋላም ሳኦል ወደ ቤቱ ተመልሶ ሄደ፤ ዳዊትና ተከታዮቹም ወደሚሸሸጉበት ስፍራ ተመለሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን እንግዲህ ከእኔ በኋላ ዘሬን እንዳትነቅል ከአባቴም ቤት ስሜን እንዳታጠፋው በእግዚአብሔር ማልልኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ለሳኦል ማለለት፥ ሳኦልም ወደ ቤቱ ሄደ፥ ዳዊትና ሰዎቹም ወደ አምባው ወጡ። |
እንግዲህ እኔንና ልጆቼን፣ ዘሬንም በመሸንገል አንዳች ክፉ ነገር እንዳታደርስብን በእግዚአብሔር ፊት ማልልኝ። እኔ ለአንተ ቸርነት እንዳደረግሁ፣ አንተም ለእኔና በእንግድነት ለተቀመጥህባት ለዚህች ምድር ቸርነት አድርግ።”
ከርሱ ዘሮች ሰባት ወንዶች ልጆች ይሰጠን፤ እኛም ከእግዚአብሔር በተመረጠው በሳኦል አገር በጊብዓ በእግዚአብሔር ፊት እንስቀላቸው” ብለው መለሱለት። ስለዚህ ንጉሡ፣ “ዕሺ እሰጣችኋለሁ” አለ።
ንጉሥ ዳዊት በራሱና በሳኦል ልጅ በዮናታን መካከል በእግዚአብሔር ፊት ስላደረጉት መሐላ ሲል የሳኦልን ልጅ፣ የዮናታንን ልጅ ሜምፊቦስቴን ከሞት አተረፈ።
ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፣ “ልጄ ዳዊት ሆይ፤ የተባረክህ ሁን፤ ታላቅ ነገር ታደርጋለህ፤ በርግጥም ይከናወንልሃል” አለው። ስለዚህም ዳዊት ወደሚሄድበት ሄደ፤ ሳኦልም ወደ ቤቱ ተመለሰ።