La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 18:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሳኦል ከቀድሞው ይልቅ ፈራው፤ እስከ ዕድሜውም ፍጻሜ ድረስ ጠላቱ ሆነ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሳኦል ከቀድሞው ይልቅ ዳዊትን ፈራው፤ እስከ ዕድሜ ልኩም ጠላቱ ሆነ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም ሳኦል ዳዊትን ይበልጥ ከመፍራቱ የተነሣ በኖረበት ዘመን ሁሉ የዳዊት ጠላት ሆነ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን አጥ​ብቆ ፈራው፤ ሳኦ​ልም ዕድ​ሜ​ውን ሁሉ ለዳ​ዊት ጠላት ሆነ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሳኦልም ዳዊትን አጥብቆ ፈራው፥ ሳኦልም ዕድሜውን ሁሉ ለዳዊት ጠላት ሆነ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 18:29
10 Referencias Cruzadas  

እንዲሁም ጥረትና የሥራ መከናወን ሁሉ ሰው በባልንጀራው ላይ ካለው ቅናት እንደሚመነጭ ተመለከትሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።


ከዚያ ቀን ጀምሮም፣ ሊገድሉት አሤሩ።


አንድ እግዚአብሔር እንዳለ ታምናለህ፤ መልካም ነው፤ አጋንንትም ይህንኑ ያምናሉ፤ በፍርሀትም ይንቀጠቀጣሉ።


እግዚአብሔር ከርሱ ተለይቶ ከዳዊት ጋራ ስለ ሆነ፣ ሳኦል ዳዊትን ፈራው።


ሳኦልም፣ ዳዊት እንደ ተሳካለት ባየ ጊዜ ፈራው፤


ሳኦል እግዚአብሔር ከዳዊት ጋራ እንደ ሆነና ልጁ ሜልኮልም እንደ ወደደችው በተረዳ ጊዜ፣


የፍልስጥኤማውያን ጦር አዛዦች እንደ ወትሮው ሁሉ፣ ለጦርነት ይወጡ ነበር፤ ዳዊትም ከቀሩት የሳኦል መኳንንት የበለጠ ድል አገኘ፤ ስሙም የታወቀ ሆነ።