1 ሳሙኤል 15:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ፣ አማሌቃውያን በመንገድ ላይ ስለ ተቃወሙት እቀጣቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ፥ አማሌቃውያን በመንገድ ላይ ስለ ተቃወሙት እቀጣቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ አማሌቃውያን በመንገድ ላይ እየተቃወሙ አስቸግረዋቸው ስለ ነበረ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አማሌቃውያንን ለመቅጣት ወስኖአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤል ከግብፅ በወጡ ጊዜ በመንገድ እንደ ተዋጉ በእስራኤል ላይ ክፉ ያደረጉትን አማሌቃውያንን ዛሬ እበቀላለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ አማሌቅ በመንገድ እየተቃወመ ያደረገበትን እበቀላለሁ። |
ከእንግዲህ ማንም ሰው ባልንጀራውን፣ ወይም ወንድሙን፣ ‘እግዚአብሔርን ዕወቅ’ ብሎ አያስተምርም፤ ከትንሹ ጀምሮ እስከ ትልቁ፣ ሁሉም እኔን ያውቁኛልና፤” ይላል እግዚአብሔር። “በደላቸውን ይቅር እላለሁ፤ ኀጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስብም።”