1 ሳሙኤል 14:48 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጀግንነት ተዋግቶ አማሌቃውያንን አሸነፈ፤ እስራኤልንም ይዘርፏቸው ከነበሩት እጅ ታደጋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጀግንነት ተዋግቶ አማሌቃውያንን አሸነፈ፤ እስራኤልንም ይዘርፏቸው ከነበሩት እጅ ታደጋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጀግንነትም ተዋግቶ የዐማሌቅን ሕዝብ እንኳ ሳይቀር ድል መታ፤ እርሱም እስራኤላውያንን ከጠላቶቻቸው እጅ አዳነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ጀግና ነበረ፤ አማሌቃውያንንም መታ፤ እስራኤልንም ከዘራፊዎቹ እጅ አዳነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ጀግና ነበረ፥ አማሌቃውያንንም መታ፥ እስራኤልንም ከዘራፊዎቹ እጅ አዳነ። |
ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “ሲታወስ እንዲኖር ይህን በጥቅልል መጽሐፍ ላይ ጻፈው፤ ኢያሱም መስማቱን አረጋግጥ፤ ምክንያቱም የአማሌቃውያንን ዝክር ከሰማይ በታች ፈጽሜ እደመስሳለሁ” አለው።
አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ዙሪያ ካሉት ጠላቶችህ ሁሉ ባሳረፈህ ጊዜ፣ ከሰማይ በታች ያለውን የአማሌቅን መታሰቢያ ደምስስ፤ ከቶ እንዳትረሳ!