እግዚአብሔር አሞራውያንን ለእስራኤል አሳልፎ በሰጠባት ዕለት፣ ኢያሱ እግዚአብሔርን በእስራኤል ፊት እንዲህ አለው፤ “ፀሓይ ሆይ፤ በገባዖን ላይ ቁሚ፤ ጨረቃም ሆይ፤ በኤሎን ሸለቆ ላይ ቀጥ በዪ።”
1 ሳሙኤል 14:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያች ዕለት እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ከማክማስ እስከ ኤሎን ድረስ ከመቷቸው በኋላ እጅግ ዝለው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያች ዕለት ፍልስጥኤማውያንን ከሚክማስ እስከ አያሎን ድረስ ከመቷቸው በኋላ ሕዝቡ እጅግ ዝለው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን እስራኤላውያን ከሚክማስ እስከ አያሎን ባለው መንገድ ሁሉ እያሳደዱ በመውጋት ፍልስጥኤማውያንን ድል መቱ፤ በዚህም ጊዜ እስራኤላውያንም በራብ እጅግ ዝለው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ፍልስጥኤማውያንን በማኪማስ መቱአቸው፤ ሕዝቡም እጅግ ደከሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ፍልስጥኤማውያንን ከማክማስ እስከ ኤሎን ድረስ መቱአቸው፥ ሕዝቡም እጅግ ደከሙ። |
እግዚአብሔር አሞራውያንን ለእስራኤል አሳልፎ በሰጠባት ዕለት፣ ኢያሱ እግዚአብሔርን በእስራኤል ፊት እንዲህ አለው፤ “ፀሓይ ሆይ፤ በገባዖን ላይ ቁሚ፤ ጨረቃም ሆይ፤ በኤሎን ሸለቆ ላይ ቀጥ በዪ።”
ሳኦል ከእስራኤል ሦስት ሺሕ ሰዎች መረጠ። ሁለቱ ሺሕ በማክማስና በኰረብታማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋራ፣ አንዱ ሺሕ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋራ ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደ የቤታቸው እንዲሄዱ አሰናበተ።
ሕዝቡ ከጠላቶቻቸው እጅ ከወሰዱት ምርኮ ዛሬ በልተው ቢሆን ኖሮ ምንኛ በተሻለ ነበር፤ የተገደሉትም ፍልስጥኤማውያን ቍጥር ከዚህ በበለጠ ነበር።”