1 ሳሙኤል 14:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡ ወደ ጫካው በገባ ጊዜ፣ የማሩ ወለላ እየተንጠባጠበ መውረዱን አየ፤ ሆኖም መሐላውን ፈርቶ ስለ ነበር፣ እጁን ወደ አፉ የዘረጋ ማንም አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡ ወደ ጫካው በገባ ጊዜ፥ የማሩ ወለላ እየተንጠባጠበ ወደ ምድር መውረዱን አየ፤ ሆኖም መሓላውን ፈርቶ ስለ ነበር፥ እጁን ወደ አፉ የዘረጋ ማንም አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዛፉ ሁሉ ማር. የሞላበት ቢሆንም የሳኦልን ርግማን በመፍራት ከማሩ የቀመሰ ማንም አልነበረም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም ማር ወደ አለበት ቀፎ ሄዱ፤ እርስ በርሳቸውም ይነጋገሩ ነበር። እነሆም፥ ሕዝቡ መሐላውን ፈርቶ ነበርና ማንም እጁን አንሥቶ ወደ አፉ አላደረገም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም ወደ ዱር በገባ ጊዜ እነሆ፥ የሚፈስስ ማር ነበር፥ ሕዝቡ መሐላውን ፈርቶ ነበርና ማንም እጁን ወደ አፉ አላደረገም። |
ጻድቃንና ኃጥኣን፣ ደጎችና ክፉዎች፣ ንጹሓንና ርኩሳን፣ መሥዋዕት የሚያቀርቡና የማያቀርቡ፣ የሁሉም የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ አንድ ነው። ለደጉ ሰው እንደ ሆነው ሁሉ፣ ለኀጢአተኛውም እንዲሁ ነው፤ ለሚምሉት እንደ ሆነው ሁሉ፣ መሐላን ለሚፈሩትም እንዲሁ ነው።