1 ሳሙኤል 12:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሳሙኤል ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “ሙሴንና አሮንን የመረጠ፣ የቀድሞ አባቶቻችሁንም ከግብጽ ያወጣ እግዚአብሔር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ሳሙኤል ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “ሙሴንና አሮንን የመረጠ፥ የቀድሞ አባቶቻችሁንም ከግብጽ ያወጣ ጌታ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም የሚናገረውን ቃል በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “ሙሴንና አሮንን የመረጠ፥ የቀድሞ አባቶቻችሁንም ከግብጽ ምድር ያወጣ እግዚአብሔር ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ሕዝቡን አለ፥ “ሙሴንና አሮንን ያላቀ፥ አባቶቻችሁንም ከግብጽ ምድር ያወጣ እግዚአብሔር ምስክር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም ሕዝቡን አለ፦ ሙሴንና አሮንን ያላቀ፥ አባቶቻችሁንም ከግብጽ ምድር ያወጣ እግዚአብሔር ነው። |
ሙሴና አሮን ካህናቱ ከሆኑት መካከል ነበሩ፤ ሳሙኤልም ስሙን ከጠሩት መካከል አንዱ ነበረ፤ እነርሱ ወደ እግዚአብሔር ተጣሩ፤ እርሱም መለሰላቸው።