1 ሳሙኤል 12:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ሳሙኤል ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ በዚያ ዕለት እግዚአብሔር ነጐድጓድና ዝናብ ላከ። ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርንና ሳሙኤልን እጅግ ፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ሳሙኤል ወደ ጌታ ጮኸ፤ በዚያኑ ዕለት ጌታ ነጐድጓድና ዝናብ ላከ። ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ ጌታንና ሳሙኤልን እጅግ ፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ሳሙኤል ጸለየ፤ እግዚአብሔርም በዚያኑ ዕለት ነጐድጓድና ዝናብ ላከ፤ ከዚህም የተነሣ ሕዝቡ እግዚአብሔርንና ሳሙኤልን እጅግ ፈሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፥ እግዚአብሔርም በዚያ ቀን ነጐድጓድንና ዝናብን ላከ፤ ያንጊዜም ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርንና ሳሙኤልን እጅግ ፈሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፥ እግዚአብሔርም በዚያን ቀን ነጎድጓድና ዝናብ ላከ፥ ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርንና ሳሙኤልን እጅግ ፈሩአቸው። |
ስለዚህ በሦስት ቀን ውስጥ የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤ በዘጠነኛው ወር በሃያኛውም ቀን ሕዝቡ ሁሉ ስለ ወቅቱ ጕዳይና ስለ ከባዱ ዝናብ በመጨነቅ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀምጠው ነበር።
ሙሴና አሮን ካህናቱ ከሆኑት መካከል ነበሩ፤ ሳሙኤልም ስሙን ከጠሩት መካከል አንዱ ነበረ፤ እነርሱ ወደ እግዚአብሔር ተጣሩ፤ እርሱም መለሰላቸው።
እስራኤላውያን እግዚአብሔር በግብጻውያን ላይ ያደረገውን ታላቅ ኀይል ባዩ ጊዜ፣ እግዚአብሔርን ፈሩ፤ በእግዚአብሔርና በባሪያው በሙሴም አመኑ።
እግዚአብሔር አሞራውያንን ለእስራኤል አሳልፎ በሰጠባት ዕለት፣ ኢያሱ እግዚአብሔርን በእስራኤል ፊት እንዲህ አለው፤ “ፀሓይ ሆይ፤ በገባዖን ላይ ቁሚ፤ ጨረቃም ሆይ፤ በኤሎን ሸለቆ ላይ ቀጥ በዪ።”
በዚያች ዕለት እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደረገው፤ ሕዝቡ ሙሴን እንዳከበሩት ሁሉ፣ ኢያሱንም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ አከበሩት።